የተፈናቃዮች ሮሮ በካማሺ ዞን
ረቡዕ፣ ጥር 10 2015በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ተፈናቅለው በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት 2014 ዓ.ም ወደ እየቀዬያቸው የተመለሱ ዜጎች ይሰጣችኋል ተብለው ቃል የተገባላቸው ሰብአዊ ድጋፍ በመቋረጡ ለችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ። በዘላቂነት እስኪቋቋሙ ድረስ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም ከሐምሌ 8 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍ እንዳላገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ (DW)ተናግረዋል። ወደ ቀዬያቸው ሲመለሱ ቀድሞ የነበራቸው ንብረት መውድሙንም ገልጠዋል። የካማሺ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ጀርሞሳ ተገኘ ወደ ቀዬያቸው ለተመለሱ ዜጎች ድጋፍ እንዳልደረሳቸው ገልጸው በእጀባ ድጋፍ እንዲመጣ ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማሳወቃቸውን ተናግረዋል። በካማሺ ዞን ከሔምሌ 2014 ዓ.ም ወዲህ 128ሺ ሰዎች ወደ ቀዬያቸው መመለሳቸውን ጠቁመዋል።
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በክልል ደረጃ 38 ሚሊዩን ብር እንሚያሰፈልገው የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም አደረኩ ባለው ጥናት ማረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡ በካማሺ ዞን ተፈናቅለው የነበሩት ከመቶ ሺ በላይ ዜጎች ከሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም አንስቶ ወደ ቀአያቸው መመለሳቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወደ ቀያአቸው ተመልሰው የሚገኙትና ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በዞኑ እንዴ ሚዥጋ፣አጋሎ የተባሉ ወረዳዎች የቁሳቀሱስ እጥረትና ይሰጣችሁዋል የተባሉት ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በካማሺ ዞን አምስት በሚደርሱት ወረዳዎች ውስጥ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በካማሺ ከተማ መጠያ ውስጥ የቆዩ ሲሆን ለሁለት ዓመት ያህል በግብርና ስራ ላይ ሳይሰማሩ መቆየታቸውን ወደ ያሶና አጋሎ መጢ የተባሉ ወረዳዎች የተመለሱት ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የካማሺ ዞን የኮሙኑኬሽን ጉዳዩች ጽህፌት ቤት ተወካይ አቶ ጀርሞሳ ተገኘ በዞኑ አምስት ወረዳዎች ውስጥ የሰላም ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ከሐሌም ወር ወዲህ 128ሺ ሰዎች ወደ ቀያአቸው መመለሳቸውን አብራርተዋል፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ አስመልክቶም በመንገድ ችግር ምክንያት አለመዳረሱን ጠቁመዋል፡፡ ወደ ቀአያቸው የተመለሱ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እና ድጋፍ ለማቅረብ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር በኩል ጥናት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በሁሉም መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ዜጎች ወደየ ወረዳወቸው መመለሳቸውን ገልጸው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ እንዲያቀርብ ዞኑ መጠየቁንም አክለዋል፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በስክልና በአካል ወደ ተቋማቸው በመሄድ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡ ከዚህ ቀደም የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በክልል ደረጃ መልሶ ለማቋቋምና የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን አስመልክቶ በሰጡን ምላሽ በሁሉም ስፍራዎች ለሚገኙት ተፈናቃዩች ርዳታ በመንገድ ችግር ምክንያት ከዚህ ቀደም ዘግቶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ዛሬ በጉዳዩ ላይ በሰጡን ማብራሪያ ለካማሺ ዞን ሰብአዊ ድጋፍ በመንገድና ጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይላክ መቆየጡን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ስር በሚገኘው ሴዳል ለተባለ ወረዳ በቅርቡ ድጋፍ መድረሱን ገልጸው በሚቀጥሉት 20 ቀናት ሰብአዊ ድጋፍ ለሁሉም ወረዳዎች እንደሚዳረስ አክለዋል፡፡
በግንቦት ወር /2014 ዓ.ም 150ሺ የሚደርሱት ወደአቀየቸው ተመልሶ በምርት ስራ ላይ መሳተፋቸውን ከኮምሽኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በክልል ደረጃ ሁሉም ወደየቀአቸው ተመልሶ በያሉበት ሆነው እንደሚደገፉ ተገልጸዋል።
ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ