1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስከ አሁን የምግብ አቅርቦት ለንም

ማክሰኞ፣ የካቲት 5 2016

በኪረሙ ወረዳ ጨፈ ሶሮማ ከምትባል ስፍራ በ2014 ዓ.ም እንደተፈናቀሉ የነገሩን እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ ነዋሪ በወረዳቸው ለረጅም ጊዜ የቆየ ጸጥታ ችግር ባሁኑ ወቅት መረጋጋቱን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ለዓመታት በቆየው የሰላም መናጋት ሀብት ንብረታቸው መውደሙን ገልጸው ሰብአዊ ድጋፍ ለወራት እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ከተማ በከፊል
ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ከተማ በከፊልምስል Privat

የተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪ

This browser does not support the audio element.

በኪረሙ ወረዳ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ለወራት ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን አስታወቁ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ለወራት ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናገሩ፡፡ በኪረሙ ወረዳ የጸጥታ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ቢሻሻልም ሰብአዊ ድጋፍ ግን እየመጣላቸው እንዳልሆነ ነው የተናሩት፡፡ ከወረዳው አቅራቢያ ተፈናቅለው በከተማ ውስጥ ተጠልለው ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የገለጹ ሲሆን ከመስረከም ወር ወዲህ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር ከ62ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር እና ሰብአዊ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች አለመቅቡን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ወይም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አረጋግጠዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 37ሺ የሚደርት ዜጎች በመጠለያ እንደሚገኙየወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ በላይ ቴናግረዋል፡፡

ሰብአዊ ድጋፍ ለወራት አልተሰጠም

በኪረሙ ወረዳ ጨፈ ሶሮማ ከምትባል ስፍራ በ2014 ዓ.ም እንደተፈናቀሉ የነገሩን እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ ነዋሪ በወረዳቸው ለረጅም ጊዜ የቆየ ጸጥታ ችግር ባሁኑ ወቅት መረጋጋቱን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ለዓመታት በቆየው የሰላም መናጋት ሀብት ንብረታቸው መውደሙን ገልጸው ሰብአዊ ድጋፍ ለወራት እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

በኪረሙ ወረዳ ጨፈ ሶሮማ ከምትባል ስፍራ በ2014 ዓ.ም እንደተፈናቀሉ የነገሩን እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ ነዋሪ በወረዳቸው ለረጅም ጊዜ የቆየ ጸጥታ ችግር ባሁኑ ወቅት መረጋጋቱን ገልጸዋል፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

‹‹ ወደ ቤታች ተመልሳችሁ ትሰራችሁ ተብሎ ተነግሮናል፡፡በአካባቢው የሰላም ሁኔታ ከበፊቱ የተሻለ ነው ድጋፍ የሚባል ነገር ግን የለም‹‹

ሌላው ሀሳባቸውን ያጋሩን የኪረሙ ነዋሪ በበኩላቸው ባለፉት ሶስት ዓመታት በአካባቢው አርሶ አደሩ በግብርና ስራ ባመሳተፉ ሰብአዊ ድጋፍ በእጅጉ እንደሚሹ ገልጸዋል፡፡ በወረዳው ከሚገኙ 19 የሚደርሱ ቀበሌዎች ውስጥ ሰዎች ተፈናቅለው በወረዳው ከተማ ውስጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ከሶስት ዓመት ወዲህ ያረሰና ምርት ያለው ሰው የለም። ከብቶች ተዘርፈዋል፣ ሌሎች ንብረትም ተወስዷል፡፡ ብዙ ሰዎች እየተቸገሩ ነው ንብረታችን በሙሉ ወድሟል፡፡ ‹‹

በኪረሙ ወረዳ ቦቃ ከምትባል ቀበሌ ተፈናቅለው እንደነበር የነገሩን ሌላው ነዋሪም ከወረዳው ከተማ አቅራቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች እየተመለሱ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በወረዳው የጸጥታ ሁኔታ ቢሻሻልም ከኪረሙ ነቀምቴና ቡሬ የሚወስዱ መንገዶች አለመከፈታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አብዛኛው ነዋሪ ከ2 ዓመት በላይ በጊዜያዊ መጠለያ የቆዩ በመሆኑ ሰብአዊ ድጋፍ አሁንም እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡

በኪረሙ ወረዳ ቦቃ ከምትባል ቀበሌ ተፈናቅለው እንደነበር የነገሩን ሌላው ነዋሪም ከወረዳው ከተማ አቅራቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች እየተመለሱ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ምስል Alemenw Mekonnen/DW

በወረዳው ከ37ሺ በላይ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ

በምስራቅ ወለጋ የኪረሙ ወረዳ የቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ በላይ በወረዳቸው ባለፉት 3 ዓመታት 62ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በወረዳው በ19 ቀበሌዎች ውስጥ 2ሺ የሚደርሱ ቤቶች መውደማቸውን አመልክተዋል፡፡ በተለያዩ ምክንያች ሰብአዊ ድጋፍ አለመቅረቡንም ገልጸው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ዜጎችን በዘላቂነት የማቋቋም ስራ ይሰራል ብሏል፡፡

‹‹ ሠላም የሰፈናባቸው ቦታዎች በተለይም ወደ ኪረሙ ወረዳ ከተማ አቅራቢያ ያሉ እየተመለሱ ነው፡፡ ሆኖም ህዘቡ ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ አሁን በወረዳው የሚገኙት ያልተመለሱ 37ሺ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ንብረታቸው ወድመው መልሶ ግንባታና ማቋቋም የተጀመረባቸው 8 ቀበሌዎች አሉ፡፡ እነዚሁ ቀበሌዎች ብዙ ሰዎች የሚኖሩባቸው ትልልቅ ቀበሌዎች ሲሆኑ የነዋሪው ንብረት በሙሉ የወደመባቸው ናቸው፡፡ ሰብአዊ ድጋፍ በቅርቡ በወረዳችን በኩል አልቀረበም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በአንድ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ቀርቦ ነበር፡፡

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ወረዳዎች ለረጅም ጊዜ በነበረው ጸጥታ ችግር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር ሲዘገብ ቆይቶአል፡፡ በአካባቢው ሲደርሱ በነበሩው ጥቃቶች በሰው እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የሰብአዊ መብት ተቋማት በተለያዩ ወቅቶች ሲገልጹ ቆይተዋል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW