የተፈናቃዮች የአዲስ ዓመት ምኞትና ተስፋ
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2018
ማስታወቂያ
ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለውበአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ተፈናቃዮች አዲስን ዓመትን በቀያቸው በናፍቆትና በፍቅር ሲቀበሉት እንደነበርና እንደወግና ባህላቸው ህፃናትን አዲስ ልብስ በማልበስ፣ ቀኑን ያደምቁ እንደነበር ዛሬ ላይ ሆነው ያስታውሳሉ፣ አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ በመጠለያ ድንኳን ለማሳለፍ ተግድደዋል፣ በደቡብ ወሎ ዞን ጃሪና መካነ ሠላም፣ በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ፣ በሰሜን ሸዋ ወይንሸት፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቀበሮ ሜዳ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም ምኞትና ያላቸውን ተስፋ ለዶይቼ ቬሌ ገልፀዋል፡፡በአማራ ክልልከትግራይ፣ ከኦሮሚያና ከቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈናቀሉ 640 ሺህ ያክል ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡
ዓለምነው መኮነን
ማንተጋፍቶት ስለሺ