1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ በሽታን የመቋቋም አቅም

ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2012

በሰዎች ሰውነት ውስጥ በሽታን መቋቋም የሚያስችል አቅም አላቸው። የበሽታ መከላከል አቅሙ ሲፈለግ ወዲያው የሚገኝ ሳይሆን በአመጋገብ እና በአኗኗር ዘይቤ እንደሚዳብር የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በመላው ዓለም ስጋት ያስከተለው የኮሮና ተሐዋሲ የተሻለ በሽታ የመቋቋም አቅም ያላቸውን ሰዎች ሕይወት እስከመቅጠፍ ሊያሰጋ አይችልም እየተባለ ነው።

Infografik Abwehrsystem des Menschen ENG

የኮሮና ተሐዋሲ ስጋት

This browser does not support the audio element.

የዓለም የጤና ድርጅት በምህፃሩ WHO ኮቪድ 19 የሚል መጠሪያ የሰጠው የኮሮና ተሐዋሲ እስካሁን ከ140 ሃገራትን በላይ አዳርሷል። በተሐዋሲው በርከት ያሉ ሰዎች የተያዙባቸው ሃገራትም የስርጭቱን ፍጥነት እና ስፋት ለመከላከል የሰዎችን እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ ከመወሰን አንስቶ የተለያዩ የጥንቃቄ ርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። በዚህ መሃልም እያንዳንዱ ሰው በየግሉ ሊያደርገው የሚገባው ጥንቃቄ ይመከራል። ተሐዋሲው የሚያስከትለው ጉዳት ከሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅም ጋር እንደሚገናኝ ይነገራል።

ሰዎች በተፈጥሮ በሰውነታቸው ውስጥ በሽታን መቋቋም የሚያስችል አቅም አላቸው። የበሽታ መከላከል አቅሙ ድንገት ስለፈለጉት ወዲያው የሚገኝ ሳይሆን በሂደት በአመጋገብ እና በአኗኗር ዘይቤ እየዳበረ የሚበለፅግ የተፈጥሮ ፀጋ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ያሳስባሉ። ከሰሞኑ በመላው ዓለም ስጋት ያስከተለው የኮሮና ተሐዋሲ የተሻለ በሽታ የመቋቋም አቅም ያላቸውን ሰዎች ሕይወት እስከመቅጠፍ ሊያሰጋ እንደማይችል ሳይንቲስቶች ተናግረዋል። በእነሱ ስሌትም አንድ ሰው በተሐዋሲው ቢያዝም በሽታውን የመቋቋም አቅሙ ጠንካራ ከሆነ የመሞት ዕድሉ አንድ በመቶ ነው።  በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ በግል ክኒሊካቸው የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ አጠቃላይ እና የውስጥ ደዌ ሀኪም ዶክተር ሊበን በሽር አልክሆል መጠጦች እና ትንባሆ ማጨስ የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅምን እንደሚያሳጡ አመልክተዋል። ስለሰውነት የበሽታ መከላከል አቅም የህክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW