1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቱሪዝም ሳምንት በኦሮሚያ እንዴት እያለፈ ነው?

ሥዩም ጌቱ
ሐሙስ፣ መስከረም 22 2018

ቴዎድሮስ ተሾመ የቱሪዝም ዘርፉ ባለድርሻ አካል በሆነው በቦረና አስጎብኚና የመኪና ኪራይ ድርጅት ስራ አስከያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው ለመጀመሪያ ጊዜተሳታፊ በሆነበት የኦሮሚ ቱሪዝም ኮሚሽን የተዘጋጀው የቱሪዝም ሳምንት አውደ ርዕይ ላይ አግኝተን አነጋግረናቸዋል፡፡

የቱሪዝም ሳምንት በኦሮሚያ እንዴት እያለፈ ነው?
የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት እየተከበረ ነው ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት እና የዘርፉ ተዋንያን ሚና

This browser does not support the audio element.

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት 

ቴዎድሮስ ተሾመ የቱሪዝም ዘርፉ ባለድርሻ አካል በሆነው በቦረና አስጎብኚና የመኪና ኪራይ ድርጅት ስራ አስከያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው ለመጀመሪያ ጊዜተሳታፊ በሆነበት የኦሮሚ ቱሪዝም ኮሚሽን የተዘጋጀው የቱሪዝም ሳምንት አውደ ርዕይ ላይ አግኝተን አነጋግረናቸዋል፡፡ “በዚህ መድረክ ላይ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት እንዲሁም ከአገር ውስጥም በርካታ ድርጅቶች የተሳተፉበት አውደርዕ ስለሆነ ጥሩ የገቢያ ትስስር ፈጥሮልናል” ሲሉ የመድረኩን ጠቃሚነት አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ አየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ ትልቅ የቱሪዝም ዘርፉ አጋር ሆኖ የሚሰራው የአቢሲንያ የበረራ አገልግሎት እና አዢየሽን አካዳሚ በዚህ የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት በሚል በኦሮሚያ  ቱሪዝም ኮሚሽን በተዘጋጀው አውደርዕ ላይ ከተሳተፉ በርካታ ደርጅቶች ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ አቶ አስረስ አያለው ድርጅቱን ወክለው በሰጡን አስተያየት የመጀመሪያቸው በሆነው በዚህ መድረክ ተሳትፎያቸው ዋናው ዓላማ ያደረጉት አዲስ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መዳረሻን ማስተዋወቅ ነው፡፡ “ኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ላይ ስንሳተፍ ይህ የመጀመሪያችን ሲሆን አዲስ ጀመርነው አገልግሎት ስላለን እሱን ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልን ስላገኘነው ነው” በማለት ይህም በቅርቡ ግንባታው ወደ ተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ጎብኚዎችን በአየር ትራንስፖርት ማጓጓዝ መጀመራቸው እንደሆነ አስረድተውናል፡፡

ቱሪዝም እና ፀጥታ

ጭስ አልባ ኢንደስትሪ በሚል ስሙ የሚታወቀው የቱሪዝም ኢንደስትሪ ዘርፍ በአይነተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ዘርፍ ብቆጠርም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በተከሰተው ግጭት ዘርፉ ይነስም ይብዛ በበርካታ ስፍራዎች ላይ በብዙ መፈተኑን ባለድርሻ አካላቱ ይጠቁማሉ፡፡ የቦረና አስጎብኚና የመኪና ኪራይ ድርጅት ስራ አስከያጅ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ፤ “እውነት ለመናገር እኛ አሁን ፍላጎት ስላለን ነው ቱሪዝም ላይ የምንሰራው” በማለት ዘርፉን የሚፈትኑ ጉድለቶች ግን እንደማይጠፉ አስረድተዋል፡፡ “አሁን ባለው ሁኔታ የሰላሙ ይዞታ አንዱ ፈታኝ ነገር ነው” የሚሉት የዘርፉ ባለሙያ የተቀዛቀዘውን የውጭ ጎብኚ በአገር ውስጥ ጎብኚዎች ለመተካት ብሰራም የግንዛቤ ማስጨበጡ ስራ ግን ገና የሚቀር እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡ “ባለፉት አምስት-ስድስት ዓመታት በቱሪዝሙ ዘርፍ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ የቆየው የጸጥታው ችግር ከባለፈው 2017 ዓ.ም. ጀምሮ አንጻራዊ ተስፋን ማሳየት ጀምሯልም” በማለት እንደ ወንጪ እና ባሌ ተራሮች ያሉ ሰላማዊ አከባቢዎች ብሎም እንደ ባቱ እና ላንጋኖ ያሉ አንጻራዊ ሰላም ያለባቸውቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች የተሻለ መዳረሻ ሆነው ስለማገልገላቸው ገልጸዋል፡፡

የአየር በረራዎች እድል

አቢሲንያ ፍላይት ተወካዩ አቶ አስረስ ግን ይህ በተለያዩ አከባቢዎች የታየው የጸጥታው ችግር የቱሪዝምን ዘርፍ በመጉዳቱ ረገድ እንደተጫወተው ሚና ሁሉ አይነተኛ እድልም ይዞ የመጣ ነው ይላሉ፡፡ “በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ላይ የሚታየው የጸጥታ መደፍረስ እንደ አገር አሳዛኝ ነገር ቢሆንም ያ ለኛ ግን እድልም ፈፈጥሮልናል” የሚሉት አቶ አስረስ፤ ብዙዎች በአየር ለመጓዝ ምርጫቸው ማድረጋቸው ወደ ተለያዩ የቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ስፍራ የሚያደርሱ መዳረሻዎች መበጀታቸው ሰፊ በረራ እድሎችን እንደፈጠረ አስገንዝበዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሰፊ ስራ ለሚጠብቀው የቱሪዝም ዘርፉ ቀሪ ሰወራዎችን በማመላከት አንድ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ተደርጎ የሚወሰድ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡   

በኢሬቻ መዳረሻ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ብሎም በመላው አገሪቱ ያሉትን የቱሪዝም እድሎችን የማስተዋወቅና ገቢያውን የመፍጠር እድልን ታሳቢ አደድርጎ በኦሮሚያ  ቱሪዝም ኮሚሽን የሚዘጋጀው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ዘንድሮ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ስካሄድ በዘርፉ ላይ ያሉትን እድሎችና ፈተናዎቹን የሚለዩ የተባሉላቸው የፓናል ውይይቶችም ተከናውኖበታል፡፡
ስዩም ጌቱ 
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሀመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW