1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርኩ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት ምንነት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 3 2017

በጋራ መግለጫው መሠረት ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ቱርክ በመጪው የካቲት ወር ውይይት ለማድረግ ከሥምምነት መድረሳቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። በዘገባው መሠረት ውይይቱ በአራት ወራት ውስጥ ሊጠናቀቅ ታቅዷል። ስምምነቱ የሶማሊያን የግዛት አንድነት፣ የሚያከብር እና ኢትዮጵያ የባሕር በር ብታገኝ ሊኖር የሚችለውን ጠቀሜታ እውቅና የሚሰጥ ይሆናል።

Türkei vermittelt Abkommen zwischen Somalia und Äthiopien zur Beendigung des Territorialstreits
ምስል DHA

የቱርኩ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት ምንነት

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለለመፍታት  “ቴክኒካዊ ውይይት” ለማድረግ መስማማታቸውን ሁለቱን ሀገራት ስታሸማግል የቆየችው የቱርክ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን አስታውቀዋል ።የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶኻን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና km,ሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ ጋር ትላንት ረቡዕ በተናጠል ከተነጋገሩ በኋላ ሦስቱ ሀገሮች በአንድ የጋራ መግለጫ ላይ ተስማምተዋል። 

ለሦስተኛ ዙር ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት በቱርክ
በጋራ መግለጫው መሠረት ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ቱርክ በመጪው የካቲት ወር ውይይት ለማድረግ ከሥምምነት መድረሳቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። በአገባው መሠረት  ውይይቱ በአራት ወራት ውስጥ ሊጠናቀቅ ታቅዷል። ስምምነቱ የሶማሊያን የግዛት አንድነት፣ የሚያከብር እና ኢትዮጵያ የባሕር በር ብታገኝ ሊኖር የሚችለውን ጠቀሜታ እውቅና የሚሰጥ ይሆናል።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የቀጠለው ውዝግብ

ስለ ቴክኒካዊው ስምምነት ምንነትና ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የባህር በር ለማግኘት ከሶማሌላንድ ጋር ስለ ተፈራረመችው  “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” እጣ ፈንታ ለንደን የሚገኙትን የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ አብዱራህማን ሰዒድ በስልክ የተደረገላቸውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ። 

ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW