የቱርክ ትብብር እና የአውሮጳ ኅብረት ጥያቄ
እሑድ፣ ጥቅምት 7 2008ማስታወቂያ
የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ቱርክ ኢስታንቡል ውስጥ ባደረጉት ንግግር ፤ቱርክ የአውሮጳ ኅብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ በዚህ ዓመት አዲስ የመደራደሪያ ምዕራፍ መክፈቱን ገልጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለቱርክ ዜጎች የቪዛ አሰጣጡ ቀለል ያለ እና የተቀላጠፈ እንዲሆን መንገድ እንደሚያመቻቹ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተናግረዋል። በአፀፌታው ታዲያ ቱርክ ስደተኞች ወደ ሀገሯ የሚላኩበትን መንገድ እንድታመቻች አንጌላ ሜርክል ከቱርክ ጠቅላይ ሚንሥትር አኅመት ዳቩቶሉ ጋር ባደረጉት ንግግር ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሀገራቸው ቱርክ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በመቆጣጠር ጀርመንን እንደምትተባበር ቃል ገብተዋል። ሆኖም «የሶሪያ ግጭት መፍትኄ ሳይበጅለት የስደተኞች ቀውስን መፍታት አይቻልም» ሲሉ አክለዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ