1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድርና ሙሌት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከሳምንታት በፊት በግብጽ ተደርጎ ፣ በቀጣይም መስከረም መጨረሻ 2016 ዓ. ም አዲስ አበባ ላይ እንዲቀጥል ቀጠሮ ተይዞለታል። በግብጽ ተደርጎ በነበረው ውይይት የግድቡ የውኃ አለቃቀቅ እና አሞላል ላይ ደንብ ማዘጋጀት በሚቻልበት ፍሬ ጉዳይ ላይ ድርድር ስለመደረጉ ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በከፊል
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር አራተኛ ሙሌት "በተገቢው እና በተያዘለት  ጊዜ ይከናውናል" ሲል የሐገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ፎቶ፤ታላቁ የህዳሴ ግድብ በከፊል ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ለ4ኛ ዙር በቅርቡ ትሞላለች

This browser does not support the audio element.

 

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር አራተኛ ሙሌት "በተገቢው እና በተያዘለት  ጊዜ ይከናውናል" ሲል የሐገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ከዶቼ ቬላ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱጡት አስተያየት መሠረት በተቀመጠው ጊዜ ይከናወናል" ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግድቡ የፊታችን መስከረም እንደሚሞላ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታዉቀዉ ነበር።
ከሰሞኑ ግብጽ ላይ የተደረገው የሕዳሴ ግድብ ድርድር በውኃ አለቃቀቅ እና አሞላል ላይ ደንብ ማዘጋጀት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ እንደነበር እና በቀጣይም መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሦስቱ ሀገሮች አዲስ አበባ ላይ ለድርድር እንደሚቀመጡ ይጠበቃል። 

                                                                                   የድርድሩ ቀጣይነት 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከሳምንታት በፊት በግብጽ ተደርጎ ፣ በቀጣይም መስከረም መጨረሻ 2016 ዓ. ም አዲስ አበባ ላይ እንዲቀጥል ቀጠሮ ተይዞለታል። በግብጽ ተደርጎ በነበረው ውይይት የግድቡ የውኃ አለቃቀቅ እና አሞላል ላይ ደንብ ማዘጋጀት በሚቻልበት ፍሬ ጉዳይ ላይ ድርድር ስለመደረጉ ለማወቅ ተችሏል።
ይሁንና ከሰሞኑ በግብጽ በኩል ኢትዮጵያ የመተባበር ፍላጎት እያሳየች አይደለም በሚል በመገናኛ ብዙኃን እየቀረበባት ያለ ወቀሳ መኖሩ ተጠቅሶ ጥያቄ የቀረበላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም "ድርድሩን ከሚዲያ ጋር ማድረግ አንፈልግም" በማለት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ መፈታት የሚችለው በመግባባት ብቻ መሆኑን እና የኢትዮጵያም አቋም ይሄው መሆኑን ለጋዜጠኞች ጠቅሰዋል። 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከሳምንታት በፊት በግብጽ ተደርጎ ፣ በቀጣይም መስከረም መጨረሻ 2016 ዓ. ም አዲስ አበባ ላይ እንዲቀጥል ቀጠሮ ተይዞለታል። ፎቶ፤ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ግዙፍ ግድብ-ሕዳሴምስል Amanuel Sileshi/AFP/Getty Images

ግብጽየድርድሩን ጉዳይ ከአፍሪካ ሕብረት ባሻገር በሌሎች አካላት እንዲዳኝ የማድረግ ያልተቋረጠ ጫና እና ግፊት አድርጋለች። ከሰሞኑ ድርድር ከተደረገበት ሥፍራ ጋር ተያይዞም አፍሪካ ሕብረት የያዘው የአደራዳሪነት ሚና ጫና ውስጥ ስለመግባቱ በታዛቢዎች ተነስቷል። ይሁንና አሁን እየተደረገ ያለው ድርድር በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተደረገ ካለው ውጪ ስላለመሆኑ እና በዚህ ረገድ ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ ተገልጻል። 

                                                                                      ግብጽ ፓለቲካዊ መልክ ያላበሰችው ግድብ 

በግድብ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ፣ የደህንነት እና የአለም አቀፍ ጫና ምክንያት እንዲሆን የተደረገ ግድብ ቢኖር ይህ የሕዳሴ ግድብ ስለመሆኑም በባለሙያዎች ዘንድ ይነገራል።
ግንባታው በኢትዮጵያ በኩል በውኃ ሚኒስቴር የሚመራ እና የቴክኒክ ጉዳይ ተደርጎ የሚታይ ሲሆን በግብጽ በኩል ግን ከፍተኛ የደህንነት እና የፀጥታ ጉዳይ ተደርጎ የተያዘ ብሎም ጉዳዩ በሀገሪቱ የደህንነት መሥሪያ ቤት ቀጥታ የሚመራ መሆኑ ማሳያ ተደርጎ ይጠቀሳል።
የግድቡ የመጀመርያ ዙር አራተኛ ሙሌት መቼ እንደሚከናወን የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተከታዩን መልሰዋል።
"በተገቢው እና በተቀመጠለት ጊዜ ይከናውናል"
ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ጉባኤ በሶማሊያ ሞቀዲሾ ዛሬ መጀመሩን፣ ይህም ትልቅ የአጋርነት መገለጫ እንደሆነም ገልፀዋል።

በግድብ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ፣ የደህንነት እና የአለም አቀፍ ጫና ምክንያት እንዲሆን የተደረገ ግድብ ቢኖር ይህ የሕዳሴ ግድብ ስለመሆኑም በባለሙያዎች ዘንድ ይነገራል። ፎቶ፤ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በከፊልምስል Gioia Forster/dpa/picture alliance

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW