የኅዳሴ ግድብ ከሚገኝበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነዋሪዎች አስተያየት
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2017
ማስታወቂያ
የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ እና የተለያዩ አፍሪካ መሪዎች እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል። የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎችም በግድቡ ግንባታ መጠናቀቅና ምርቃት ላይ ደስታቸውን ገልጸዋል። የግድቡ መጠናቀቅን ከአድዋ ድል ጋር በማመሳሰል የገለጹት ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በተለይም ለክልሉ ወጣቶች እና ሕዝብ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን አብራርተዋል። ግድቡ ለኢትዮጵያ ኩራት መሆኑን ያወሱት ነዋሪዎቹ፣ በተለይም ወጣቶች በግድቡ አካባቢ በሚፈጠሩት የሥራ እድሎች ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ