«የታሰረዉ የሃገሬ ታሪክ ይፈታ» ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
እሑድ፣ የካቲት 18 2010ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሰሞን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አድዋን በተመለከተ ባለፈዉ ሰሞን በአዲስ አበባ ራስ ትያትር ፖየቲክ ጃዝ ምሽት መድረክ ላይ ያቀረበዉ የድምፅ ሥራ በማኅበራዊ መገናኛ ተለቆ በርካቶችን ሲያወያይ ፈገግ ሲያሰኝ ሰንብቶአል። ዲያቆን ዳንኤልን እስቲ ስለዚህ ስራህ እናዉራ አልነዉ እሺ አለ በሙሉ ልብ፤ ከዝግጅት ክፍላችን በባህላዊ በማኅበራዊ ብሎም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ለትብብር ጥያቄ ሲቀርብለት ከመተባበር ወደኃላ ብሎ አያዉቅምና ዛሬም በማመስገን ቃለ ምልልሳችን ጀመርን። መጀመርያ ዲያቆን ዳንኤል ይህን ሥራህን አንተ ነህ ወይስ ሌሎች ናቸዉ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የለቀቁት? እዉቅናስ ሰተሃቸዉ ነበር? ስንል ጠይቀነዉ ነበር። በአዲስ አበባ ራስ ትያትር ያቀረበዉ ጽሑፍ ርዕስ «አድዋ በጎሰኞች ዓይን» ይሰኛል። ከዲያቆን ዳንኤል አዝናኝና እና ምክራዊ ቃለ ምልልስ ሰጥቶናል፤ ሙል መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ