1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሰሩ ተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት ይዞታ

ሐሙስ፣ መስከረም 3 2016

በአማራ ዋና ዋና ከተሞች ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ሸዋ ሮቢት እንዲሁም በአፋር አዋሽ አርባ የሚገኙ ናቸው በተባሉት ማቆያ ስፍራዎች ተይዘዉ ይገኛሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች 764 ናቸው ሲል ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት መግለጫ የሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን አፈፃፀም እንዲመረምር የተዋቀረው መርማሪ ቦርድ አስታውቋል።

በአስቸኳይ አዋጁ መሠረት ከታሰሩት መካከል መካከል የከፋ ግፍና በደል ተፈፅሞባቸዋል የታባሉ ሰዎች ምስል በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መሰራጨቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣ አስከትሏል።
ፎሮ ማህደር እስር ቤት በአፍሪቃምስል Cellou Binani/AFP

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ መግለጫ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከደነገገ ካለፈዉ ኃምሌ ማብቂያ እስከ ጳጉሜ 3 2015 ድረስ በጥርጣሬ የታሰሩት ሰዎች ቁጥር 764 መሆኑን የዐዋጁን አፈፃፀም እንዲመረምር የተዋቀረው ቦርድ አረጋገጠ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የተባለዉ ኃይል ባለፈዉ ማክሰኞ ባወጣዉ መግለጫም የታሰሩት ተጠርጣሪዎች 764 መሆናቸዉን አስታዉቆ ነበር።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተጠርጣሪዎች ከሚገኙባቸዉ ማቆያ ጣቢያዎች የጎበኘዉ አንዱን ብቻ እንደሆነ ገልጧል። በአስቸኳይ አዋጁ መሠረት ከታሰሩት መካከል መካከል የከፋ ግፍና በደል ተፈፅሞባቸዋል የታባሉ ሰዎች ምስል በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መሰራጨቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣ አስከትሏል።እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ "የተለያዩ ፎቶዎችን እየለጠፉ የሕጻናትና የዐዋቂዎች የማገቻ ካምፖች ናቸው የሚባሉት ቦታዎች ፈጽሞ እውነት ያልሆኑ የፈጠራ ዜናዎች ናቸው" ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ መሰል ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን በመግለጽ በሂደት ያለውን ሁኔታ አመሳክሮ ውጤቱን እንደሚገልጽ አስታውቋል።
"የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ የማገቻ ካምፕ የለውም" 

ፎቶ ከማህደር፤ እስር ቤት በአፍሪቃምስል Amr Nabil/AP Photo/picture alliance

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በዚህ ሳምንት በጽሑፍ ባወጣው መግለጫ በዐዋጁ ምክንያት ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን ለማቆያነት "እስካሁን ያዘጋጃቸው የማቆያ ቦታዎች 5 ብቻ ናቸው" በማለት ገልጿል።
በአማራ ዋና ዋና ከተሞች ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ሸዋ ሮቢት እንዲሁም በአፋር አዋሽ አርባ የሚገኙ ናቸው በተባሉት ማቆያ ስፍራዎች ተይዘዉ ይገኛሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች 764 ናቸው ሲል ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት መግለጫ የሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን አፈፃፀም እንዲመረምር የተዋቀረው መርማሪ ቦርድ አስታውቋል።
የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንደሞ "ይሄ ቁጥር ሊጨምር ሊቀንስ ይችላል" ብለዋል። 
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ክትትል 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እስካሁን ድረስ ከተዘጋጁት ማቆያዎች ውስጥ በአዋሽ አርባ በአካል በመገኘት የታሰሩትን 53 ወንድ እስረኞች ብቻ መጎብኘቱን ገልጾ ወደ ሌሎች ቦታዎች አለመጓዙን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሬኬብ መለሰ ገልፀዋል።
"ሌሎቹን ለማየት አብዛኞቹ አማራ ክልል የሚገኙ በመሆኑና በግጭት እና የመረጋጋት ሁኔታው አምቺ ስላልሆነ እነሱን መጎብኘት እልቻልንም። ቁጥሩ ትክክለኛ ነው ትክክለኛ አይደለም ብሎ ለማለት የሚያስችል መረጃም የልንም" ብለዋል።የ33 የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና የሲቪል ማሕበራት ተቃውሞ
ታሳሪዎችን በተመለከተ እየወጡ ያሉ ፎቶዎች እና የመንግሥት ምላሽ   

ፎቶ ከማህደር፤ እስር ቤት ምስል Colourbox

በሌላ በኩል በተለይ "በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ማቆያ ስፍራዎች የተነሱ ናቸው" በሚል በማህበራዊ መገናኛዎች እየወጡ ያሉ ፎቶዎች አነጋጋሪ ሆነዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ዕዝ "የተለያዩ ፎቶዎችን እየለጠፉ የሕጻናትና የዐዋቂዎች የማገቻ ካምፖች ናቸው የሚባሉት ቦታዎች ፈጽሞ እውነት ያልሆኑ የፈጠራ ዜናዎች ናቸው" ብሏል ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ። "በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ምክንያት ሰዎችን ከዕዙ ዕውቅና ውጭ ማሠርና ማገት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው" ያለው ዕዙ መንግሥት ይህ ዓይነት ፍላጎት የለውም ብሏል።
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጥቆማ እየደረሳቸው መሆኑን በመግለጽ በሂደት አጣርተው እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ እውቅና ውጪ ተይዘው ይታሰራሉ ስለሚባሉ ሰዎች ጉዳይ የፌዴራል ፖሊስ ምን ይላል የሚለውን የጠየቅናቸው የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጀላን አብዲ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW