1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታቀደው የብሔራዊ ምክክር ላይ የፖለቲከኞች አስተያየት

ሐሙስ፣ የካቲት 3 2014

ባለፈው ብሔራዊ ምርጫ ተሳትፎ ያልነበራቸውና በተለይም በኦሮሚያ ክልል በሰፊው የሚንቀሳቀሰው በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በብሔራዊ ምክክሩ አሳታፊነት ላይም ከወዲሁ ጥያቄ አንስተዋል።

Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed im Parlament
ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

«ኦነግ እና ኦፌኮ አሳታፊነቱ ላይ ጥያቄ አንስተዋል»

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ በቀጣይ እንደሚደረግ በሚጠበቀው የብሔራዊ ምክክር ሂደት ላይ እምነት እንደሌላቸው ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች አስታወቁ። ባለፈው ብሔራዊ ምርጫ ተሳትፎ ያልነበራቸውና በተለይም በኦሮሚያ ክልል በሰፊው የሚንቀሳቀሰው በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በብሔራዊ ምክክሩ አሳታፊነት ላይም ከወዲሁ ጥያቄ እያነሱ ነው። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የፖለቲካ ድርጅቶቹ ኃላፊዎች ብሔራዊ ምክክሩን ለማሳለጥ የሚቋቋመው ኮሚሽን ተፈላጊውን ውጤት እንዲያመጣ የኮሚሽነሮች ገለልተኝነት እና የምክክሩ ሁሉን አሳታፊ መሆን ለድርድር መቅረብ የለበትም ይላሉ።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW