1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታኅሣሥ 26 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2013

ባሳለፍነዉ የ2020 ዓ.ም በዓለማችን በተከሰተዉ የኮሮና ወረርሽኝ ሳብያ በርካታ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ስፖርታዊ ዉድድሮች በመሰረዛቸዉ ሳብያ ዓመቱ ለኢትዮጵያዉያን አትሌቶች እንዴት አልፎ ይሆን? የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የታላቁ ሩጫ ፤ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ዉድድር ይካሄዳል።

Fußball Bundesliga Bayern München - Mainz 05
ምስል Andreas Gebert/AFP/Getty Images

በአዉሮጳዉያኑ የገና እና የአዲስ ዓመት በአላት ምክንያት ተቋርጠዉ የነበሩት አንዳንድ የአዉሮጳ የእግር ኳስ የሊግ ዉድድሮች ወደ ሜዳ ተግባር በመመለስ ላይ ሲገኙ በጀርመን ቡንደሊስ ሊጋ የአምናዉ ሻንፒዮና ባየር ሙኒክ በአዲሱም ዓመት ኃያልነቱን ቀጥሎበታል። ሜንዝ 05 ን አምስት ለሁለት ( 5 -2 ) በሆነ ዉጤት ሲረታ፤ የዓለማችን የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ሮበርት ሊቫዶቭስኪም ጎል ማምረቱን ተያይዞታል። ዶርትሙንድም በሳምንቱ መጨረሻ ደረጃዉን አሻሽሎአል። በእንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት ወሳኝ ፍልምያ ይጠብቀዋል። ዘረኝነትን የተላበሰ መልዕክትን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቅመህ አስተላልፈሃል በሚል በእንጊሊዝ የእግርኳስ ፌደሬሽን የሦስት ጨዋታዎች ቅጣት የተጣለበት ኤድሰን ካቫኒን  ያላሰለፈዉ ማንችስተር ዩናይትድ አስቶን ቪላን በማሸነፉ በደረጃዉ ሰንጠረዥም ሁለተኝነት ላይ ለመቀመጥ ችሎአል።

ምስል Wendemagegn Getachew/DW

ባሳለፍነዉ የ2020 ዓ.ም በዓለማችን በተከሰተዉ የኮሮና ወረርሽኝ ሳብያ በርካታ ዓለምአቀፋዊ እና አህጉራዊ ስፖርታዊ ዉድድሮች መሰረዛቸዉ እና ወደ ሌላ ጊዜ በመዛወራቸዉ ሳብያ ዓመቱ ለኢትዮጵያዉያን አትሌቶች እንዴት አልፎ ይሆን? በዚሁ ጉዳይ ላይ ከኢትዮ-ራነርስ ፋን ከተሰኘዉ ድረ-ገጽ አዘጋጅ ከሆነዉ  ከወንድማቸዉ ጌታቸዉ ጋር ቆይታ አድርገናል። የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የሚካሄደዉ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የ10 ኪሎሜትር ዉድድርን በተመለከተ አዘጋጆችን አነጋግረናል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ነጋሽ መሐመድ

   

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW