የታንዛኒያ ዴሞክራሲ እና የታጠፈው የፕሬዚደንቷ ቃል
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 11 2016በታንዛኒያ በቅርቡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ ፖለቲከኞች እና ተንታኞችን ጨምሮ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ምህዳር ወዴት ይወስደው ይሆን ሲሉ አሳስቧቸዋል።
የፊታችን ሰኞ ከሚከበረው አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በፊት ፖሊስ ታዋቂውን ፖለቲከኛ ቱንዱ ሊሱ እና ሌሎች አራት የቻዴማ ፓርቲ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አውሏል። እሁድ እለት ፓርቲው ያዘጋጀው የወጣቶች የድጋፍ ሰልፍ ግርግርና ብጥብጥ ይፈጥራል በሚል ስጋት ባለስልጣናት ከልከላ ጥለው ነበር ።
በወቅቱ ለእስራት ተዳርገው የነበሩት በዋስ ቢለቀቁም ነገር ግን ክስተቱ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሀሰን የፖለቲካ ተቀናቃኞቿ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ በገቡት ቃል ላይ ንቀት የፈጠረ መስሏል።
የታንዛኒያ ህገ-መንግስት የዜጎችን ነፃነት በማረጋገጥ የመናገር እና በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ ነፃነትን ይሰጣል ። ነገር ግን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ይህን ደስታ አላገኙም ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ጎድዊን ጎንዴ አማኒ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
ታንዛንያ የመጀመርያዋን ሴት መከላከያ ሚኒስትር ሾመች
«ችግሩ የሚመጣው የመናገር ነፃነትን ትርጉም እና ባለስልጣናት ሰዎች እንዴት ሀሳባቸውን መግለጽ እንዳለባቸው የሚፈልጉበት መንገድ ነው። እና በዚህ ደግሞ ጥቂት ሰዎች ከሌሎቹ የበለጠ ነፃነት ሲያገኙ ታይቷል»
ፕሬዚደንት ሳሚያ ሃሰን በቀድሞው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ጥለዋቸው የነበሩ ዕገዳዎችን በማንሳት በማጉፉሊ የፕሬዝዳንትነት ዘመን ያልነበረውን የፉክክር ፖለቲካ ወደ ሀገሪቱ ለመመለስም ቃል ገብተው ነበር።
ነገር ግን ነገሮች ለፕሬዚዳንቷ እንደቃላቸው አልጋ በአልጋ አልሆኑላቸውም።
በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ነዋሪ የሆኑት ቢያትሪስ ባንዴዋ ለDዶቼ ቬለ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንቷ በእስካሁኑ ጉዟቸው ጥሩ እምነት አሳይተዋል። ስለዚህ በቅርቡ በተከሰቱ ክስተቶች ሊመዘኑ አይገባቸውም ይላሉ ።
ታንዛኒያ ኢትዮጵያዉያን እስረኞችን ልትለቅ ነዉ
በጎርጎርሳዉያኑ 2021 ፕሬዝዳንት ሳሚያ ወደ ስልጣን በመጡ ጊዜ ሁሉም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች በሀገሪቱ ውስጥ እንዲከናወኑ ፈቅደዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም ህጎችን እና መመሪያዎችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል” ስትል ተናግራለች።
ለባንዴዋ ዋና ጉዳይ ይህ አይደለም። "በየትኛዉም የፖለቲካ ሰልፎች ሁሉም ሁሉም ለመልካም ነገር አይወጣም። አንዳንዶች የጥላቻ ንግግር በማሰማት እና ብጥብጥ ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው።" ይላሉ
የሀገሪቱ ፖሊስ የፊታችን ሰኞ ሊካሄድ የታቀደውን ሰልፍ መከልከላቸው አዘጋጆቹ ሰዎች ልክ እንደ ኬንያ ወጣቶች እንዲወጡ በመጠየቃቸው እንደሆነ ተዘግቧል።
አዘጋጆቹ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የ2024 የፋይናንስ ረቂቅ ህግ እንዲፀድቅ ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የተከተለው ህዝባዊ አመፅ ስልጣናቸውን እንዲለቁ መጠየቃቸው በማሳያነት ጠቅሰዋል።
የታንዛኒያ ምርጫ፣ የካሜሩን እገታ
በፖሊስ ድርጊት የማይስማማው ታንዛኒያዊ ዊልያም ማዱሁ እንደሚሉት፣ የመንግስት መጨረሻው እርምጃ በታንዛኒያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ደጋፊዎቻቸው ጉልህ የሆነ ግፍ እንዲፈጸም ፣ የዘፈቀደ እስራት እና ሌሎች የፖለቲካ ስደት ሲደርስባቸው ወደ ነበረበት ጨለማው ዘመን መመለሱን ያሳያል ። በተለይ ደግሞ ወደ ማጉፉሊ ዘመን። ይህንንም ሲገልጹ “እነዚያ የ17 ዓመታት የጨለማ ዓመታት እንደገና የመመለስ ያህል ናቸው።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተካሂዶ በነበረ ህዝባዊ ስብሰባ ወቅት የታንዛኒያ ገዥው የመሃል ግራው ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (ሲሲኤም) ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ኢማኑኤል ንቺምቢ የፖሊስ እርምጃ ስጋት ነበራቸው። በተቃዋሚዎች እና በገዥው ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ሊያከሽፉ ይችላሉ የሚልም ስጋት አድሮባቸዋል።
ነገሮቹን በውይይት ለመፍታት ለፖለቲከኞች እድል ይስጠን ሲሉ ተደምጠዋል።
አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡት አማኒ እንደሚሉት በቅርቡ በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የፖለቲካ ውጥረቶችን ለመቀነስ የታለመውን የእርቅ ጥረት ሊያደናቅፍ ይችላል።
በፕሬዚዳንቱ እና ከእርሳቸው ቀ,ድመው በነበሩ የፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ወቅት ከነበሩ ጊዜያት ጋር ሲነፃፀሩ ብዙ ነገሮች እየተቀየሩ ነው።
አሁን የእርቅ ጉዳዮች አሉ ፤ በተቃዋሚዎች እና በገዥው ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባትንም የመፍታት ጉዳዮች አሉ።
አማኒ አያይዘው ፖሊስ እና ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች ስልጣናቸውን እና ተልእኮአቸውን ከመጠን በላይ እየተጠቀሙ ነው ሲሉ ይተቻሉ።
"በናይጄሪያ እና በኬንያ የተከሰተው ነገር የትኛውንም ሀገር ሊጎዳ ይችላል እና ታንዛኒያ ከዚህ ብዙ መማር አለባት።»
በቅርቡ በሀገሪቱ መንግስት የተወሰደው እርምጃ ከምርጫው በፊት ማንኛውንም አይነት የሁከት ድርጊት ለመከላከል ብቻ ስለሚመስላቸው አግባብነት የለውም ተብሎ ሊወሰድ አይገባም ሲሉ ባንዳዌ ይናገራሉ።
ማጉፉሊ፣ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ
«እንደምናውቀው በዚህ አመት ሀገሪቱ ለአካባቢ አስተዳደር ምርጫ ታካሂዳለች። የመንግስት አካላት እነዚህን የፖለቲካ ሰልፎች እና ተቃውሞዎች የማይፈቅዱትም በዚህ ምክንያት ነው "
የዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተመልካቹ ቡድን ባለፈው ረቡዕ ባወጣው መግለጫ የታንዛኒያ ፖሊስ ዋነኛው የመንግስት ተቀናቃኝ ፓርቲ አባላት የሆኑ 375 ሰዎችን በዘፈቀደ ማሰሩን አስታውቋል።
አማኒ እንደሚሉት ታንዛኒያ የዴሞክራሲ ምህዳሯን ነጻነት አጎናጽፋ ለብዝኃ አመለካከቶች እና እንቅስቃሴዎች መፍቀድ አለባት ። ታንዛኒያ "በፖለቲካው መጫወቻ ሜዳ ውስጥ መቻቻል እንዲኖር መፍቀድ አለባት ምክንያቱም ሰዎች ሁል ጊዜ አንድ ዓይነት ማሰብ አይችሉም" ።
ካልዴዚ ኢዛክ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ