1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከታንዛኒያ ምርጫ ግጭት በኋላ ፖሊስ የወሰዳቸው ርምጃዎች እየወጡ ነው

ልደት አበበ/ Lidet Abebe
ዓርብ፣ ኅዳር 5 2018

የታንዛንያን ምርጫ ተከትሎ በሐገሪቱ በተነሳው ብጥብጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ዋናው የተቃዋሚ ፓርቲና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይናገራሉ። የታንዛንያ መንግስት የተጠቀሰው ቁጥር የተጋነነ ነው ቢልም ስለሞቱ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ከመግለፅ ተቆጥቧል። የታንዛኒያ ፖሊስ ርምጃን በተመለከተ ዶይቸ ቬለ የቪዲዮ ዘገባ ሰርቷል።

Tansania Stone Town 2025 | Polizist stoppt Mann wegen Wahlmanipulation
ምስል፦ Marco Longari/AFP

ከታንዛኒያ ምርጫ ግጭት በኋላ ፖሊስ የወሰዳቸው ርምጃዎች እየወጡ ነው

This browser does not support the audio element.

ስሙን መግለፅ ያልፈለገው ወጣት ታንዛኒያዊ የገጠመውን ነገር እስካሁን ማመን ተስኖታል። የ 32 ዓመቱ ወጣት በታንዛኒያ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ማግስት ነው ውኃ ሊያመጣ በወጣበት በፖሊስ ጥይት የተመታው።«ራሴን መሬት ላይ ነው ያገኘሁት። እግሬን ስመለከት ይደማል። ቀና ስል ፖሊስ ወደ እኔ አነጣጥሯል። እሄኔ ጭንቅላቴን ቢሆን ኖሮ ያገኙት አልቆልኝ ነበር።»

ዶይቸ ቬለ ለዚህ ዘገባ ጁማ ብሎ የሚጠራው ወጣት ስለገጠመው ነገር ሲናገር ይንቀጠቀጣል። «የዶይቸ ቬለ የቀረፃ ቡድን ምናልባት ሰላይ ይሆናል ብሎ ብዙ ካመነታ በኋላ ነው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለ ደረሰበት ነገር እንዲያውቅ ለመናገር የፈቀደልን» ትላለች የዶይቸ ቬለ ዘጋቢ ኤዲት ኪማኒ  
አወዛጋቢውን ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት ምን ያህል ህይወት እንደጠፋ እስካሁን ይፋ አልሆነም ሆኖም በርካታ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ኢንተርኔቱን እየሞሉ ነው። ከእነዚህ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መካከል ከባድ መሣሪያ የታጠቁ ወንዶች አደባባይ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ላይ ሲተኩሱ ይታያል። 
እንደየተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ከሆነ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  ተገድለዋል።
እኝህ የዳሬሰላም ነዋሪ የታዘቡትን ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።«ከፍተኛ  ዷ ዷ የሚል የተኩስ ድምጽ ሰማሁ።  እዚህ ጋር፤ እዛ ጋር አስከሬን ነበር።  ሌላ ደግሞ እዛ ጋር በደም የተጨማለቀ አስክሬን አየሁ።  በጣም ግራ ስለገባኝ መሮጥ እንኳን አልቻልኩም። እውነት ነው ሰዎች ሞተዋል። ብዙ ሰዎች ሞተዋል። በአይኔ አይቻለሁ።«

ምስል፦ Marco Longari/AFP

ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

ዶይቸ ቬለ ይህንን ቀረጸ በቦታው ባደረገበት ወቅት፣ የቀረፃ ቡድኑ በታጠቁ ፖሊሶች በተደጋጋሚ ቁጥጥር ተደርጎበታል። ምርጫ ከተካሄደ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በታንዛኒያ ትልቋ ከተማ ዳሬሰላም ህይወት በጥንቃቄ እና ቁጥጥር በተሞላበት ሁኔታ ቀጥሏል።  ምክትል ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ንቺምቢያ ሁሉም ነገር ደህና ነው ይላሉ። «የፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን መንግስት በሀገሪቱ ያለውን አንድነት ለመመለስ እየሰራ ይገኛል። አሁን አገራችን ተረጋግታለች ። ሁሉም ሰው የህግ የበላይነትን እያከበሩ ነው።«

በዚህ ህግ መሠረት 400 የሚጠጉ ሰዎች ከምርጫ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከእነዚህ መካከል በለጠፈችው ቪዲዮ ምክንያት  በአገር ክህደት የተከሰሰችው ቲክቶከር  ጄኒፈር ጆቪን  ናት። ቪዲዮው ላይ ቲክቶከሯ ለተከታዮቿ ባስተላለፈችው መልዕክት በምርጫ ቀን ከአስለቃሽ ጭስ እንዲከላከልላቸው ጭምብል እንዲያጠልቁ ትመክራለች። 
በእስረኞች ላይ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተቃዋሚዎች ዋና ጠበቃ ፒተር ኪባታላ ይህ የማይካድ ሀቅ ነው ይላሉ። 
« ሚስጥር አይደለም። ከባድ ስቃይ እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤት አስረድተናናል።  አንዳንዶቹ እንደውም በግልፅ የሚታይ ውጫዊ  የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።»

ምስል፦ AP Photo/picture alliance

አወዛጋቢውን ምርጫ በመቃወም በተነሳው ግጭት የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ማክሰኞ  ጥሪ አቅርቧል።  ፖሊስ ከአስክሬን ማቆያ ስፍራ የነበረ አስክሬን ወደ ማይታወቅ ቦታ መውሰዱ ከተሰማ በኋላ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር  ፎልከር ቱርክ “ማስረጃ ለመደበቅ እንደተሞከረ ግልጽ ነገር አለ” በማለት ባለስልጣናት የሟቾችን አስክሬን ለሟች ቤተሰቦች እንዲያስረክቡ እና ቀብራቸው እንዲፈፀም ጠይቀዋል።  

ልደት አበበ

ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW