1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታክሲዎች አድማ በአዲስ አበባ

ሰኞ፣ የካቲት 21 2008

አዲስ አበባ በታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ጭር ብላ ውላለች። አዲስ አበቤዎችም እግረኛ ለመሆን ተገደዋል። የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የመንግስት የሰራተኛ ማመላለሻ አውቶብሶች የታክሲ አገልግሎት ፈላጊዎችን ሲያጓጉዙ የሚያሳዩ ምስሎችም ይገኙበታል። የአዲስ አበባ የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ በአካባቢዋ የሚገኙ ከተሞችንም ማዳረሱ እየተነገረ ነው።

Äthiopien - Taxifahrer in Addis Ababa
ምስል AP

[No title]

This browser does not support the audio element.

ዛሬ በአድማዉ ላይ ከተሳተፉት መካከል የአንድ የታክሲ ሾፌርና የአንድ የታክሲ ረዳት የወጣዉን መንገድ ትራፊክ ደሕንነት ደንብ ላይ ባለመስማማት አድማ እንደመቱ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የታክሲ ንብረቶች ማህበር ሊቀ መንበበር እና የ16 ማህበሮች አስታበበሪ የሆኑት አቶ አበበ የታክሲ አሸከርካሪዎቹ ስጋት የማህበሩ ስጋት መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩ እንዲታይ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ እንዳቀረቡ ተናግሮዋል።

ዛሬ በተደረገዉ አድማ የተሳፋሪዎች ጉዞ መስቶጋጎሉን በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክ ድረ ገፅ ላይ የተወያዩት ተሳታፊዎች አስታውቀዋል። አንድአንድ አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት፣ ከሁለት እስከ 10 ክሎሜትር በእግራቸዉ ተጉዘዋል፣ ሌሎችም ወደትምህርት ቤታቸው እና ወደ ስራ ቦታቸው መሄድ ያልቻሉት ወደ ቤታቸዉ ተመልሰዋል።

ምስል DW

ሌላዉ አስተያየት ሰጭ ደግሞ አዲስ ከተማ የሚገኘው አውቶቡስ ተራም የደራ ገበያ ይመሥል ነበር ፤ ታክሲም የሚባል አልነበረም ብሏል፤ እንዳውም እሱም ራሱ ታክሢ አጥቶ ብዙ ከቆመ በኋላ ሠርቪሥ አግኝቶ ወደ ስራው አርፍዶ መሄዱን ነው የገለጸው። ከአውቶብስ ተራ እስከ ደምበል ድረስ ታክስ ያለመኖሩን ተናግሮዋል። ሌላም አስተያየት ሰጭ እንደሚለው፣ ዛሬ አጋጣሚ ሆኖ አውቶቡስ ተራ ሠው ለመሸኘት ከቤት የወጣውሁ በጠዋቱ ቢሆንm በህይወት ዘመኑ አይቶት የማ ያውቀው አይነት አስቸጋሪ የህዝብ እንግልት እንደገጠመው አመልክቶዋል። ሌላው ደግሞ እንዳለው፣ የታክሲ አይነት አይታይም፣ ከሲ ኤም እስከ አውቶቡስ ተራ ድረስ 200ብር ፈሉን ሲመለሥ ደግሞ በእግሩ ነበር የሄደው።፡

ሌላኛዉ አስተያየት ሰጭ ደግሞ ይህ ስራ አድማ በአዲስ አበባ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን በአዳማ እና በአሴላ የህዝብ አመላላሽ መኪኖች እንደተሳተፉበት አብራርቷልአዲሱን የቀላል ባቡር የተጠቀሙም የባቡሩ ተሳፋሪዎች በጣም አስቸጋሪና አጨናናቅ ነበረ ብለዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW