1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታገተቱ ተማሪዎች የት ናቸዉ?

ሐሙስ፣ ጥር 7 2012

ለፈዉ ሕዳር 24 ከደንቢዶሎ ወደ ጋምቤላ ሲጓዙ የታገቱት ባብዛኛዉ ሴት ተማሪዎች መለቀቃቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት አስታዉቀዉ ነበር።ከእገታዉ ያመለጠች አንዲት ተማሪ የጠቀሰችዉ የታጋቾች ቁጥር መንግስት የገለጠዉ ቁጥርም ይለያያል።

Karte Äthiopien englisch

የታገቱ ተማሪዎችና የወላጆች ጭንቅት

This browser does not support the audio element.

ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ የትዉልድ አካባቢያቸዉ ሲጓዙ ማንነታቸዉ ባልታወቀ ሰዎች የታገቱት የአማራ ተማሪዎች መለቀቅ-አለመለቀቃቸዉ ዛሬም እያከራከረ ነዉ።ባለፈዉ ሕዳር 24 ከደንቢዶሎ ወደ ጋምቤላ ሲጓዙ የታገቱት ባብዛኛዉ ሴት ተማሪዎች መለቀቃቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት አስታዉቀዉ ነበር።ከእገታዉ ያመለጠች አንዲት ተማሪ የጠቀሰችዉ የታጋቾች ቁጥር መንግስት የገለጠዉ ቁጥርም ይለያያል። የተማሪዎቹ ወላጆችና የአማራ መስተዳድር ተቃዋሚ ፖለተከኞች እንደሚሉት መንግሥት ሥለተማሪዎቹ መለቀቅ የሰጠዉ መግለጫ እዉነትነት እያጠራጠረ ነዉ።ተለቀቁ የተባሉት ተማሪዎች እስካሁን ከወላጅ፣ ዘመድ ወዳጅ ጋር አልተገናኙም።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW