1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትምህርት ስርዓቱ ጉድለቶች ተጽዕኖ

እሑድ፣ ሚያዝያ 2 2014

የትምህርት ፖሊሲው ትውልድ አምክኗል የሚሉት ወገኖች ፖሊሲው የተሳሳተ የሚሉትን ትርክት ማካተቱ ሀገር ይረከባል ተብሎ በሚታሰበው ወጣት ላይ የማንነት እና የስነልቡና ቀውስ አሳድሯልም ባይ ናቸው።

Äthiopien | Schüler in der Ate Sertsedingle Schule
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

እንወያይ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የትምህርት ፖሊሲ ለሀገሪቱ የትምህርት ጥራት መውደቅ በዋነኛ ተጠያቂ ሆኖ ሲተች ቆይቷል። በተማሪዎች ብቃት እንዲሁም በአንዳንድ ቦታም በመምህራን የማስተማር አቅም ላይ ሳይቀር ያስከተለው አሉታዊ ተጽዕኖ ዛሬ በየደረጃው እየታየ መሆኑን በመረጃ የሚሞግቱ አሉ። ለሳይንስ ትኩረት ይሰጣል የተባለው የትምህርት ስርዓት ዝቅተኛ ነጥብ ያገኙትን በመምህርነት እንዲሰማሩ ማድረጉ ይበልጥ ዘርፉን እንደጎዳው ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሌላ በኩል የብሔራዊ ፈተና ስርቆቶች የአደባባይ ጉዳይ ከሆኑ የተነበተ እንደመሆኑ ድርጊቱ ከማኅበረሰብ ሞራል ይዞታ ጋር ያያይዛሉ። በዚህ የትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚወጣው ተማሪ ምን ያህል ብቃት ያለው እና ኃላፊነት የሚሰማው በስነምግባርም የታነጸ ነው የሚለውን አጠያያቂ አድርጎታል። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት የትምህርት ስርዓቱ ጉድለቶች እና ተጽዕኖውን አስመልክቶ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋብዞ አወያይቷል። ሙሉ ውይይቱን ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW