1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትምህርት ቤቶች መዉደም በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2013

ኢትዮጵያን እያመሰ በሚገኘው የአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ጦርነት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል። ብዙዎችም የአካል ጉዳት ሰለባዎች ኾነዋል። በጦርነቱ ከደረሰው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ባለፈ የሐብትና ንብረት ውድመትም ተከስቷል። የመንግሥትና የግል ተቋማት ውድመትም ታይቷል።

Logo I Bildungsministerium von Äthiopien

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩ ስለተቋማት ውድመት ይናራሉ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያን እያመሰ በሚገኘው የአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ጦርነት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል። ብዙዎችም የአካል ጉዳት ሰለባዎች ኾነዋል። በጦርነቱ ከደረሰው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ባለፈ የሐብትና ንብረት ውድመትም ተከስቷል። የመንግሥትና የግል ተቋማት ውድመትም ታይቷል። የትምህርት ሚኒስቴር እንደሚለው በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች ሰባት ሺህ ትምህርት ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ትምህርት ቤቶችን ማውደም ኢትዮጵያ የምትከተለው ባህላዊ እና መንፈሳዊ እሴቶቿን ያልተቀበለ የትምህርት ሥርዓት ውጤት ነው ሲሉ አንድ የትምህርት ባለሞያ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW