1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካላቲን አሜሪካ

የትራምፕና እና የፑቲን የአላስካ ውይይት አንድምታ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 10 2017

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ አላስካ ግዛት ውይይት አካሂደዋል።ሁለቱም መሪዎች ውይይቱ «ስኬታማ ነበር» ከማለት ውጭ ስለ ውይይቱ ብዙ አላሉም። ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ቦለድሚር ዘለንስኪንንም በመጭው ሰኞ ወደ ዋይት ሀውስ ጋብዘዋል።

 የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ
የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕምስል፦ Sergei Bobylev/ZUMA/IMAGO

የትራምፕና እና የፑቲን የአላስካ ውይይት አንድምታ

This browser does not support the audio element.

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ አላስካ ግዛት ውይይት አካሂደዋል።ውይይቱን በተመለከተ በደፈናው «ፍሪያማ» ግን ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት ከማለት ውጭ በምን በምን ጉዳዮች እንደተወያዩ ሁለቱ መሪዎች በዝርዝር የተገለፁት ነገር የለም።

ውይይቱን ተከትሎ ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ «ትሩዝ ሶሻል» በተሰኘው የግላቸው የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ባሰፈሩት መልዕክት «በሩስያና ዩክሬይን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነትን ለማስቆም የተሻለው መንገድ ቀጥታዊ የሰላም ስምምነት ማድረግ ሲቻል ነው» ብለዋል።የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ውይይቱ ውጤታማ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። የዩክሬይን ጦርነትን ተከትሎ በአሜሪካና አውሮፓ በርካታ የማዕቀብ አይነቶች የተጣለባት ሞስኮ ከፕረዚደንት ትራምፕ ጋር የቀጥታ ውይይት ማካሄዷ እንደ ታላቅ ስኬት እንደሚወሰድ የሩስያ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ቦለድሚር ዘለንስኪንንም ለማነጋገር በመጭው ሰኞ ወደ ዋይት ሀውስ ጋብዘዋል

በሌላ በኩል ዩክሬንን ያላካተተ የተናጠል ውይይት ውጤታማ አይሆንም ሲሉ የቆዩት የአውሮፓ ሐገራት፤ የሁለቱን መሪዎች ውይይት ተከትሎ  በፑቲን ላይ ጫና እንዲደረግ የሚጠይቅ መግለጫ አውጥተዋል። 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
 

አበበ ፈለቀ

ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW