1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትራምፕ ርምጃና የአዉሮጶች ዛቻ

ማክሰኞ፣ የካቲት 4 2017

የትራምፕ እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅና ተሻራኪ የሆኑትን የአዉሮጳ መንግሥታትን አስደንግጧል።የአዉሮጳ ሕብረት፣የአባል ሐገራትና የብሪታንያ መሪዎች የትራምፕን እርምጃ ተቃዉሞዉ ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል

ትራምፕ አዲስ የጨመሩትን ታሪፍ በድርድር ለመፍታት የአዉሮጳ መንግስታት እየጣሩ ነዉ።ይሁድና ድርድሩ ካልሆነ አዉሮጶች አፀፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታዉቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ።ትራምፕ ከዚሕ ቀደም በተደጋጋሚ እንደዛቱት ወደ ሐገራቸዉ በሚገቡ የብረትና የአልሙኒየም ማዕድናት ላይ አዲስ ግብር ወይም ታሪፍ ጥለዋል።ምስል፦ Kevin Lamarque/REUTERS

የትራምፕ ርምጃና የአዉሮጶች ዛቻ

This browser does not support the audio element.

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕወደ አሜሪካ በሚገቡ የብረትና የአልሙኑየም ማዕዳናት ላይ የቀረጥ ጭማሪ አድርገዋል።

ትራምፕ ትናንት እንዳስታወቁት ከየትኛዉም ሐገር ወደ አሜሪካ የሚገባ ብረትና አልሙኒየም 25 በመቶ ቀረጥ ይከፍላል።

የትራምፕ እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅና ተሻራኪ የሆኑትን የአዉሮጳ መንግሥታትን አስደንግጧል።

የአዉሮጳ ሕብረት፣የአባል ሐገራትና የብሪታንያ መሪዎች የትራምፕን እርምጃ ተቃዉሞዉ ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል።ድርድሩ ካልተሳካ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ አፀፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታዉቀዋል።

ሥለ ትራምፕ ርምጃ-የአዉሮጶች ዛቻ የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW