1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ አስተዳደር ሕገ ወጥ ባላቸው ስደተኞች ላይ የያዘው ዕቅድ

ታሪኩ ኃይሉ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 10 2017

በቅርቡ በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የስደተኞች ጉዳይ፣ የተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ዋነኛ የምርጫ ቅስቀሳ አጀንዳ ነበር። ትራምፕ፤በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ወደ ፕሬዝዳንትነት ከተመለሱ ከመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ዕለት አንስቶ ህገወጥ ያሏቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ለማባረር ቃል ገብተዋል።

ቶም ሆማን
ቶም ሆማን ምስል MEGAN VARNER/AFP

የትራምፕ አስተዳደር ሕገ ወጥ ባላቸው ስደተኞች ላይ የያዘው ዕቅድ

This browser does not support the audio element.

የትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ቃልኪዳን

በቅርቡ በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የስደተኞች ጉዳይ፣ የተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ዋነኛ የምርጫ ቅስቀሳ አጀንዳ ነበር። ትራምፕ፤በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ወደ ፕሬዝዳንትነት ከተመለሱ ከመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ዕለት አንስቶ ህገወጥ ያሏቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ከአሜሪካ ምድር ለማባረር ቃል ገብተዋል።  ቀጣዩ ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ይህንኑ የምርጫ ዘመቻ ቃልኪዳናቸውን እንዲያስፈጽሙላቸውም፣ቶም ሆማንን ለወሳኙ ስራ "የድንበር ዛር" አድርገው መርጠዋቸዋል።

መጪው የትራምፕ አስተዳደር፣ይህን ዕቅዱን እንዴት ሊያስፈጽም እንደሚችል እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን፣ጉዳዩ በተለይ ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በአሜሪካ በሚኖሩ ስደተኞች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።

"መሬት አንቀጥቅጥ" ዕርምጃ

በቨርጂኒያ ግዛት የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ፍጹም አቻምየለህ፣ትራምፕ ሊወስዱት  የተዘጋጁትትን ዕርምጃ፣"መሬት አንቀጥቅጥ" ሲሉ ገልጸውታል። "እንግዲህ አሁን ዶናልድ ትራምፕ ከጃንዋሪ ጀምሮ ስልጣን ሲይዙ፣በኢምግሬሽን ጉዳይ የሚወስዱት እርምጃ፣ላለፉት 67-70 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ዕርምጃ ነው፤መሬት አንቀጥቅጥ እርምጃ ነው ተብሎ ነው የሚፈራው። የሕግ ባለሙያው፤  መጨው የትራምፕ አስተዳደር ስደተኞችን በተመለከት ሊወስድ የሚችላቸውን ጠበቅ ያሉ ዋና ዋና ዕርምጃዎች በተመለከተ እንደሚከተለው አብራርተዋል።

" ዋና ዋናዎቹ ምንድነው፣እስከ ዛሬ አንድ ሰው ከዚህ አገር ውጣ ተብሎ የሚባረረው፣ በፍርድ ቤት የመሰማት መብቱ ተከብሮ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ የፍርድ ቤቱ ከዛም የኢሚግሬሽን ቦርድ ይግባኝ ሰሚ፣ውጣ ብሎ የመጨረሻው ዉሳኔ ሲወስን ነው።ዶናልድ ትራምፕያንን የመሰማት መብት ፍርድ ቤት የመቅረብን መብት አስቀርተው ያለምንም የፍርድ ቤት የመሰማት መብት፣በፍጥነት የማባረር፣ሁለተኛ የአሜሪካ ጠረፎችን በጠረፍ ጠባቂ ሳይሆን በወታደር የማስጠበቅ፣ ሦስተኛ ደረጃ ለአንድ ሰባት መቶ ሺ ሰዎች ያህል ጊዜያዊ የመቆያ ፍቃድ የሰጠውን ለኢትዮጵያ፣ኤይቲ፣ ሱማሊያና ኤልሳቫዶር ከለላ የሰጠውን  ጊዜያዊ የመቆያ ፈቃድ /ቲፒኤስን/ማስቆም ነው።"

በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያን ምን ይጠበቃል?

የትራምፕ አስተዳደር ህገወጥ ስደተኞችን በስፋት ከሃገር ለማስወጣት የያዘው ዕቅድ፣በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውን ላይ የከፋ ተፅዕኖ እንዳያስከትልም ዶክተር ፍጹም ተከታዩ ምክር አላቸውም።

" እዚህ ሃገር ወረቀት ለማግኘት ሂደት ላይ ያሉ ሰዎችና ጠበቃ የሌላቸው ጠበቃ የሌላቸው ጠበቃ እንዲይዙ፣ጠበቃ ያላቸው ደግሞ ከጠበቆቻቸው ጋር እየተመካከሩ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲነጋገሩ፣ ከሌላ ሃገር የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ለማምጣት የሚፈልጉ ሰዎች፣ትራምፕ  ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት፣ ከጠበቆቻቸው ጋር ተነጋግረው እነዛን ማመልከቻዎች ማስገባት ነው።ለዜግነት ማመልከት የሚፈልግ ሰው ዛሬ እያለ የሚጠብቅ ሰው ካለ፣ ህጋዊ ከሆነ፣ ወንጀል ከሌለው ወይም የመኖሪያ ፈቃዱን ያገኘበት መንገድ ትክክለኛ ከሆነ፣ ዜግነቱን እንዲያመልክት፣በጉዞ ሰነድ እየገባው እየወጣው እኖራለሁ ያለ ሰው፣ በትክክል ከጠበቃው ጋር ተነጋግሮ አዲስ አለም ስለሆነ የምናየው ማለት ነው፤በድሮ በሬ ማረስ የለምና፣ እያንዳንዱ ሰው ካለው ጉዳይ በተያያዘ፣ ከጠበቃው ጋር እየተመካከረ ማድረግ ያለበትን ማድረግ ነው።" ትራምፕ አስፈጽመዋለሁ በማለት የገቡት ቃል፣ወደ ከፍተኛ የገንዘብና የሎጀስቲክ ፈተናዎች ሊያመራ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቀቃሉ፤ እሳችሁ ግን የሚፈለገው ዋጋ ተከፍሎ ስራው መከናወን አለበት ባይ ናቸው።

ታሪኩ ኃይሉ 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW