የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥ በአጋምሳ ከተማ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 16 2017የአሙሩ ወረዳ አጋመሳ ከተማ ከዞኑ ከተማ ጋር የሚያገናኝ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ከ2 ዓመት በላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው አሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ከዞኑ አስዳር መቀመጫ ከሆነው ሻምቡ ከተባለው ከተማ ጋር በመንገድ ችግር እና ጸጥታ ችግር ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ለዓማት ተገድቦ መቆጡን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋ፡፡
በአካባው ለተራዘመ ጊዜ በቆየው የጸጥታ ችግር በአካባቢው ነዋሪ ላይ ተጽኅኖ እያሳደረ የሚገኝ ሲሆን ለህክምና እና ለሎች ጉዳዩች ነዋሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡ የአጋምሳ ከተማ ከንቲባ የሖኑት አቶ ጌታሁን የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ረጅም ጊዜ እንደሆነው አረጋግጠዋል፡፡ ከዞኑ አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡
ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ፤ አጋምሳ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዳግም ስራ መጀመራቸው
በሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን የአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ከዞኑ አስተዳደር መቀመጫ ከሆነችሁ ሻምቡ ከተማ በ96 ኪ.ሜ ገደማ ርቀት ላይ የሚትገኘው አሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ወደ ዞኑ ከተማ የሚወስደው የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ከ2 ዓመት በላይ እንደሆነው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በከተማው ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ከረጅም ጊዜ በኃላ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ቢሆንም ለንግድም ሆነ ወደ ሌላ አካባቢዎች መንቀሳቀስ ግን አዳጋች መሆኑን ነው ነዋሪዎች የተናገሩት፡፡
“ከአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ወደ ሻምቡ ከተማ መንገድ ዝግ ነው፡፡ በህክምና ችግር ሰዎች እየተጎዱ ነው ወደ ሌላ ቦታ ሄዴው መታከም አይችሉም፡፡ ተማሪዎች አንድ አንደ ታጅበው ይሄዳሉ የትራንስፖርት አገልግሎት በጣም አስተቸጋሪ ነው፡፡”
የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸው
ሌላው የአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ነዋሪም የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ረጅም ጊዜ እንደሆነው ተናግረዋል፡፡ ለህክምና አገልግሎት ወደ ኪረሙ ወረዳ እና ጊዳ አያና ወረዳ በሞተርና በእግር ሰዎች ይሄዱ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በዚህም አካባቢ በሚከሰቱት የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለመንቀሳቀስ ስጋት እንደፈጠረባቸው አክለዋል፡፡
“ወረዳችንን ወደ ሌላ አካባቢዎች ጋር የሚያኘው የትራንስፖርት የለም፡፡ ሰዎች ሲቸገሩ ወደ ምስራቅ ወለጋ ጊዳና ኪረሙ በእግርና በሌሎች አማራጮች ይሄዳሉ፡፡ ከሻምቡ በታች የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ አጋምሳ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡”
የአጋምሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታሁን ደሳለኝ በአጋምሳ ትራንስፖርት አገልግሎት ከተቃረጠ ዓመታትን ማስቆጠሩን ያረጋገጡ ሲሆን ለዚህ የመንገድ መበላሸትና የጸጥታ ችግር ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
“የመጓጓዣ አገልግሎት የለም አሁንም አስቸጋሪ ነው፡፡ ወደ ነቀምቴም ወደ ሆሮም የለም ዓመታትን አስቆጠረዋል፡፡ ወደ አሙሩ ወረዳ ኦቦራ ከተማ የሚወሰደውም መንገድ አልተጠገነም ችግሩን ለዞን በተደጋጋሚ አመልክተናል መፍትሄ አልተገኘም፡፡”
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳር የሆኑት አቶ ዲንሳ ዱጉማ በአካባቢው ትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የጥገና ስራ በመሰራት በላይ እንደሚገኙ አጭር የጹሑፍ መልዕክት ገልጸዋል፡፡ በአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር ሰዎች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ለንግድና ህክምና አገልግሎት ከፍተኛ ተጽህኖ ማሳደሩን ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
እሸቴ በቀለ