1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የትራንስፖርት ዘርፍ ውስብስብ ችግር ያለበት ነው» የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር

ሐሙስ፣ ሰኔ 19 2017

መንግሥት ይህንን መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ጥረት ማድረጉን የገለፁት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዚህም ያልተገባ ኬላ ወይም የፍተሻ ጣቢያ እንዲቀር ቢደረግም በየጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት አሽከርካሪን ሁለት ሁለት ሺህ ብር የሚጠይቁ ቀማኞች መኖራቸውንና ችግሩ መልኩን ቀይሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል፦ Solomon Muche/DW

«የትራንስፖርት ዘርፍ ውስብስብ ችግር ያለበት ነው» የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከቦታ ቦታ፣ ሕዝቧ የሚመገበውን የሀገር ውስጥ የግብርና ምርትም ይሁን ከውጭ የሚገባን ልዩ ልዩ ሸቀጥ በየብስ ጭነው የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎችበየዕለቱ አቤት ከሚሉባቸው ጉዳዮች አንዱ ሕገ ወጥ ኬላ ዘርግቶ ገንዘብ የሚጠይቃቸው መብዛቱ ነው፤ የፀጥታው ችግር እንዳለ ሆኖ። 

መንግሥት ይህንን መሠረታዊ ችግር ለመቅረፍ ጥረት ማድረጉን የገለፁት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዚህም ያልተገባ ኬላ ወይም የፍተሻ ጣቢያ እንዲቀር ቢደረግም በየጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት አሽከርካሪን ሁለት ሁለት ሺህ ብር የሚጠይቁ ቀማኞች መኖራቸውንና ችግሩ መልኩን ቀይሮ መቀጠሉን ገልፀዋል። ይህንን የሚፈጽሙ ሰዎች "ከክልል መስተዳድሮች ተደብቀው" እንደሚያደርጉትም ነው ዛሬ ሐሙስ ለፓርላማው የነገሩት።

"ኬላ የለም ግን ሰዎች መኪና ያስቆሙና ብር ይሰበስባለ"

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ፍሰት ማደጉን ከዚህ በፊት አስታውቋል። ሆኖም ይህ ሁኔታ የመጣው ሕብረተሰቡ በፀጥታ ችግር ምክንያት በተሽከርካሪ በየብስ ከቦታ ቦታ መጓጓዝ ባለመቻሉ የመጣ መሆኑ ተጠቅሶ ትችት ቀርቦበታል። በታዛቢዎች። ይህ የየብስ መጓጓዣ ፍሰት እና የፀጥታ ችግር እንዲቀረፍ ምን ተሠራ? የሚለው ዛሬ ከፓርላማው ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ የቀረበ ነበር። እሳቸውም ይህንን መልሰዋል።

በታኅሳስ 2017 ዓም በበሲዳማ ክልል የደረሰ የመኪና አደጋ ምስል፦ Sidama National Regional State Health Bureau/Handout via Xinhua/picture alliance

"በአብዛኛው የሀገሪቱ ሰላም እየተሻሻለ፣ ብዙ ቦታዎች አስተማማኝ ሰላም እየሰፈነ ስለሆነ ያንን ከስር ከስር እያዩ የትራንስፖርቱንም የማስጀመር ሥራ እየተሠራ ነው"በአዲስ አበባ ብዙ አሽከርካሪዎች ለደንብ መተላለፍ የሚቀጡት የገንዘብ መጠን ማደጉ የቅሬታ ምንጭ ሆኖባቸዋል። ይህ ያልተገባ የተጋነነ ቅጣት ነው በሚል የተጠየቁት ሚኒስትሩ ይህ የሚጠናከር እንጂ ወደኋላ የሚባልበት ጉዳይ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።

የትራንስፖርት ዘርፍ ውስብስብ ችግር ያለበት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በ11 ወራት በትራፊክ አደጋሕይወቱ የተቀጠፈ፣ አካሉም የጎደለው ሰው ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል። ይህም በመሆኑ የሀገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች እንደገና ተፈትነውና ለምዘና ተቀምጠው የማሽከርከር ፈቃዳቸው እዲሰጥ ሊደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለአደጋዎች ዋናው እና እስከ 70 በመቶ ተጠያቂው አሽከርካሪው ነው በማለት።

በዛሬው የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የደብረታቦር ከተማ፣ የአዊ ዞን እና የምዕራብ ሐረርጌ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎች ምላሽ ያግኙ በሚል ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። አውሮፕላን ማረፊያ በሁለት ማረፊያዎች መካከል በዓየር ላይ ርቀር 60 ኪሎ ሜትር መሆን እንዳለበት፣ አዋጭነቱ እንደሚታይ የጠቀሱት ሚኒስትሩ የቴክኒክ ድጋፍ ከማድረግ በዘለለ ግንባታው ከመሥሪያ ቤታቸው ኃላፊነት ውጪ መሆኑን ጠቅሰዋል።

 

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW