1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራይን ጊዚያዊ አስተዳደር በማረዘም ሰበብ የታየዉ ልዩነት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 23 2017

ይህ የአዋጅ ማሻሻያ በፓርላማው የፀደቀው በትግራይ የስልጣን ዘመኑ የተጠናቀቀው ግዚያዊ አስተዳደር ዕድሜ ለአንድ ዓመት ለማራዘም መታቀዱ በኢትዮጵያ መንግስት ከተነገረ በኃላ ነው። በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የሕግ መሰረት ዙርያ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የተለያየ አቋሞች እያንፀባረቁ ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ የተፈረመዉ የኢትዮጵያና የህወሓት ግጭት የማቆም ሥምምነት አተረጓጎም አሁንም ሁለቱን ወገኖች እያለያየ ነዉ።
ከሁለት ዓመት በፊት ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ የተፈረመዉ የኢትዮጵያና የህወሓት ግጭት የማቆም ሥምምነት አተረጓጎም አሁንም ሁለቱን ወገኖች እያለያየ ነዉ።ምስል፦ PHILL MAGAKOE/AFP/Getty Images

የትትግራይን ጊዚያዊ አስተዳደር በማረዘም ሰበብ የታየዉ ልዩነት

This browser does not support the audio element.

የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበት ስርዓት የሚደነግግ የማሻሻያ አዋጅ ዛሬ በኢትዮጵያ ፓርላማ ፀደቀ። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ በፓርላማው የፀደቀው በትግራይ የስልጣን ዘመኑ የተጠናቀቀው ግዚያዊ አስተዳደር ዕድሜ ለአንድ ዓመት ለማራዘም መታቀዱ በኢትዮጵያ መንግስት ከተነገረ በኃላ ነው። በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የሕግ መሰረት ዙርያ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የተለያየ አቋሞች እያንፀባረቁ ነው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው በአብላጫ ድምፅ ያፀደቀው የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበት ስርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅ፥ የፌደራል መንግስቱ በክልሎች የሚያቋቁማቸው ግዚያዊ አስተዳደሮች ለሁለት ግዜ የማራዘም ስልጣን ለአፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ የተደረገው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በአዋጅ የተፈቀደለት የስራ ዘመን ሁለት ዓመት ብቻ እንደሆነ እና ይህ ግዜም መጠናቀቁ ካስታወቁ በኃላ ነው። በ2015 ዓመተምህረት መጋቢት ወር ስራ የጀመረው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የአዋጅ ማሻሻያ እና ሌሎች ለውጦች ተደርገውበት ለአንድ ዓመት እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በቅርቡ አስተላልፈውት በነበረ መልእክት አስታውቀው ነበር።

በትግራይ የግዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ዘመንለማራዘም በፌደራል መንግስት እየተጠቀሰ የሚገኘው አዋጅ 359/1995 እንዲሁም ደንብ ቁጥር 533/ 2015 ሲሆኑ፥ እነዚህ ድንጋጌዎች ግን ህወሓት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ተቃውሟቸዋል። በትግራይ የሚቋቋም ግዚያዊ አስተዳደር በፕሪቶርያ ስምምነት አንቀፅ 10 መሰረት መሆን እንዳለበትትም በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት አቋሙ አስታውቋል።

የሕግ ምሁሩ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ በግዚያዊ አስተዳደሩ የሕግ መሰረት ዙርያ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የተለያየ አቋሞች እና የተለያየ ሀሳቦች እያነሱ መሆኑ ይገልፃሉ። ሁለቱ የተፈራረሙት የፕሪቶርያው ስምምነት በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የማቋቋም ጉዳይ በግልፅ ያስቀመጣቸው ነጥቦች መኖራቸው የሚያነሱት ያነጋገርናቸው የሕግ ምሁር አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ፥ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እና በፌደራል መግግስቱ እና ህወሓት መግባባት ለመፍጠር የውሉ ድንጋጌዎች መተግባር አስፈላጊ መሆኑ ያነሳሉ።

 

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ከሁለት ዓመት በፊት ግዚያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበት አዋጅ ሲጠቅስ ህወሓት በወቅቱ አለመቃወሙም የሕግ ምሁሩ ተችተዋል።የስራ ዘመኑ እንደተጠናቀቀ የተገለፀው በትግራይ የቆየው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ግዚያዊ አስተዳደር ለውጦች ተደርገውበት ወደ ስራ ይገባል ተብሎ የተገለፀ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ስለተደረጉ ለውጦች የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW