የትንሳኤ በዓል ዋዜማ በመቀሌ ደምቋል
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 26 2016ማስታወቂያ
መቐለ በበዓል ዋዜማው ደምቃለች። የበዓል ግብይቱ ደርቷል፣ ከተማው ሞቅ ደመቅ ብሏል። የገበያ ንረቱ ግን በርካቶች አሳስቧል።
ለሁለት ወራት በዓብይ ፆም ላይ የቆየው ህዝበ ክርስቲያን በነገው ዕለት የትንሳኤ በዓል ለማክበር በዋዜማው ላይ ይገኛል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ መቐለ፥ በዓል ዋዜማ ግብይት እና የተለያዩ ስነስርዓት ደምቃለች። ተዘዋውረን በተመለከትናቸው የመቐለ የገበያ ስፍራዎች ለእርድ የሚሆኑ በጎችና ፍየሎች፣ ደሮ እና የተለያየ አስቤዛ፣ የስጦታ እቃዎች፣ የህፃናት እና አዋቂዎች ልብስ ግብይት በስፋት ይታያል።
በአንፃራዊ ሰላም ላይ ሆነው በዓሉ የሚያከብሩ ያነጋገርናቸው የመቐለ ነዋሪዎች፥ የኑሮ ውድነቱ የገበያ ንረቱ ግን አማሯቸዋል። የበዓል ዋዜማው ከግብይት እና የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ውጭ በከተማይቱ የተለያዩ እምነት ተከታይ አብያተክርስቲያናትም እንዲሁ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች እየተከወኑ ነው።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ታምራት ዲንሳ