የትግራዩ ጦርነትና የኮሎኔሉ አስተያየት
ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራዊ መግሥት ጦር ትግራይ ዉስጥ «ሕግ ለማስከበር» ያለዉ የጦር ዘመቻ የመጨረሻ ግብ በክልሉ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ማስፈን እንደሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።በሚንስቴሩ የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ወታደራዊ ዘመቻዉ "መገባደጃና መጨረሻዉ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።የፌደራሉ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች በገጠሙት ጦርነት ሠላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እየተማፀኑ ነዉ።ኮሎኔል ሹማ እንደሚሉት ጦራቸዉ ሰላማዊ ዜጎችን ከታጣቂዎች «ለመለየት» አበክሮ ይጥራል።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ