የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሦስት ጀነራሎች ላይ የተላለፈውን እግድ ተቃወመ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 2 2017
የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሦስት ጀነራሎች ላይ የተላለፈው የእግድ ውሳኔ ተቃወመ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ሦስት ከፍተኛ የትግራይ ሐይል አዛዦች ከስራ ማገዳቸውን ተከትሎ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፥ የፕሬዝዳንቱ እርምጃ "የተቋማችን አሰራር ያልተከተለ፣ ያልሾመውን የሚያወርድ እና የተናጠል እርምጃ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም" ብሎታል። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በበኩሉ የእግድ እርምጃውን ተቃውሟል።በአዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ ምክርቤት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ተሳታፊ አይደለም
በተለይም ከጦርነቱ በኋላ በህወሓት ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል የሰፋ እና ወደሌሎችም የተሻገረ ሲሆን፥ ይህ ክፍፍል ተከትሎ የመጣው የትግራይ ሐይሎች ለአንድ የህወሓት ክንፍ ያዘነበለ ውሳኔ እና የተግባር እንቅስቃሴ ደግሞ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት ለአደጋ የሚያጋልጥ ሆንዋል ሲሉ በርካቶች በመግለፅ ላይ ናቸው። ከትግራይ ሐይሎች አመራሮች ጋር ውዝግብ ላይ ያሉት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ትላንት ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሐይሎችን አዛዦች ከስራ ማገዳቸው አስታውቀዋል። እነዚህ ሶስት የትግራይ ሐይሎች አዛዦች ሜጀር ጀነራል ዮሐንስ ወልደግዮርጊስ፣ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ እና ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ ናቸው።
በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ የተሰራጨዉ የግንባር አዛዦቹ የሚያግድ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው "ህዝባችን ወደማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ እንቅስቃሴ አሁንም አልቆመም" የሚል ሲሆን፥ መግባባት እስኪደርስ ድረስ ሦስቱ ከፍተኛ የትግራይ ሐይሎች ወታደራዊ አዛዦች "ከሰራዊት ግንባር የማዘዝ ሃላፊነታቸው" ላልተወሰነ ግዜ እንደታገዱ ያመለክታል።
በተመሳሳይ ትላንት ለመገናኛ ብዙሐን መግለጫ የሰጡት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ የመንግስት አቅም ተጠቅመው መንግስት የማፍረስ እንቅስቃሴ ላይ የተጠመዱ ከፍተኛ አዛዦ አሉ ሲሉ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት ጌታቸው "የመንግስት ሐይል ተጠቅመህ መንግሰት ለማውረድ የሚደረግ ጥረት አደገኛ ነው ብቻ ሳይሆን፥ ህዝባችን ካለበት መከራ ወደ ሌላ የባሰ መከራ የሚከት ስለሆነ ወንጀልም ጭምር ነው። ከዚህ ቶሎ እንውጣ። አንዳንዱ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳይቀር ድንገት ግጭት ከተቀሰቀሰ እና ከቁጥጥር ውጭ ከወጣ አንድ ነገር እናተርፋለን የሚል እንደሚኖር አምናለሁ። ይህ ስህተት ነው። በትግራይ ግጭት የሚጠቀም ትግራዋይ ሊኖር አይችልም" ብለዋል።
በትግራይ ክልል ድህነት፣ ሥራ አጥነትና የወጣቶች ስደት መበራከት
ይህ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የተላለፈ የሦስት ጀነራሎች የእግድ ውሳኔ ከትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ እንዲሁም በትግራይ ክልል ድህነት፣ ሥራ አጥነትና የወጣቶች ስደት መበራከት በዶክተር ደብረፅዮን ከሚመራ የህወሓት ክንፍ ተቃውሞ ገጥሞታል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ሦስት ከፍተኛ የትግራይ ሐይሎች አዛዦች ከስራ ማገዳቸው በደብዳቤ ማስታወቃቸው ተከትሎ ዛሬ ጠዋት መግለጫ ያወጣው የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፥ የፕሬዝዳንቱ እርምጃ "የተቋማችን አሰራር ያልተከተለ፣ ያልሾመውን የሚያወርድ እና የተናጠል እርምጃ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም" ብሎታል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ