የትግራይ ሲቢል ማሕበራት ሕብረት የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደር ወቀሰ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2017
የትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ሕብረትአዲሱ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ሁሉንም ባገለለ መንገድ የተዋቀረ ነዉ በማለት ተቸ።ከ120 በላይ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ተቋማትን ያቀፈው ሕብረት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የሚመለከታቸው አካላትን በሙሉ ባካተተ መልኩ ሊስተካከል ይገባል ብሏልም። በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታትም ብሔራዊ ጉባኤ እንዲጠራ ጠይቋል።
ኢትዮጵያበትግራይ ያለው ሁኔታ የዳሰሰ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ሲቪል ማሕበረሰብ ሕብረት እንዳለው በክልሉ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከግዜ ወደግዜ እየከፋ፣ የህዝብ አንድነት እየተከፋፈለ፣ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራ ነው የለ ሲሆን፥ ይህ ለመፍታት ሊያግዝ ይችል የነበረው በቅርቡ ዳግም ወደስራ የገባው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ደግሞ ሁሉም አካላት ያካተተ ተደርጎ ሊዋቀር ሲገባ፥ ከዚህ በተቃራኒ የሆነ መንገድ መከተሉ አመልክቷል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ካለፉት ጥንካሬዎች እና የነበሩ ድክመቶች በመገምገም፥ ሊኖሩት የሚገባ ተቋማት፣ ሊወከሉ የሚገባ የማሕበረሰብ ክፍሎች እና ሊያካትታቸው የሚገባ ተቋማት ሳይዝ፥ ከፕሪቶርያው ስምምነት ውጭ በሆነ መንገድ መመስረቱ 'ለቅቡልነቱ፣ አካታችነቱ እና ውጤታማነቱ' እንቅፋት መሆኑም ይህ የሲቪል ተቋማት ሕብረት አመልክቷል።
አንድ መቶ ሃያ አራት በትግራይ የሚንቀሳቀሱሲቪል ተቋማት ያቀፈው የትግራይ ሲቪል ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መዝገበ መሓሪ ለዶቼቬለ እንደገለፁት፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በ2015 ዓመተምህርት ሲቋቋም ጀምሮ፥ አስተዳደሩ በፕሪቶርያው ስምምነት ይዘት መሰረት እንዲሁም ሁሉም ባቀፈ መልኩ እንዲደራጅ እንደ ሲቪል ተቋማት ጥረት ሲደረግ፥ ሀሳቦች ሲቀርብ መቆየቱ የሚያነሱ ሲሆን ይሁንና ይህ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተከትሎ በርካታ ፖለቲካዊ ችግሮች በትግራይ መፈጠራቸው እንዲሁም ተባብሰው መቀጠላቸው አብራርተዋል። ዐቢይ አህመድ ዓሊበቅርቡ ለአንድ አመት ይቆያል ተብሎ የተቋቋመው በጀነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርም ቢሆን ከዚሁ የተለየ እንዳልሆነ አቶ መዝገበ ጨምረው አስረድተዋል።
በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት፣ ሁሉን አካታች ብሄራዊ ውይይት በማካሄድ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱም ሕብረቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ካልሆነ ግን በትግራይ ያለው ሁኔታ አስጊ መሆኑ የትግራይ ሲቪል ማሕበረሰብ ተቋማት ሕብረት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መዝገበ መሓሪ ገልፀዋል።
በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶችም እንዲሁ በትግራይ ስራ ላይ ያለው ግዚያዊ አስተዳደር አካታች እንዳልሆነ የሚገልፁ ሲሆን፥ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር በዚህ ከተለያዩ አካላት የሚቀርብ ወቀሳ እና ጥያቄ ዙርያ ምላሽ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ፀሐይ ጫኔ