1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ሴት ተፈናቃዮች

ረቡዕ፣ የካቲት 29 2015

የትግራይ ተፈናቃይ ሴቶች እንደሚሉት ጦርነቱ በተለይ በሴቶችና ህፃናት ላይ ያደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ ነዉ።ሴቶች እንደማንኛዉም ነዋሪ በጦርነቱ ከመጎዳታቸዉ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ተደፍረዋል፣ የተለያየ ፆታ ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋልም።

Äthiopien | Binnenvertriebene aus Tigray
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በጦርነቱ መሐል በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል

This browser does not support the audio element.

ትግራይ ዉስጥ ይደረግ በነበረዉ ጦርነት ከየቀያቸዉ የተፈናቀሉ የክልሉ ሴቶች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸዉን ይናገራሉ።ዛሬ በመከበር ላይ የሚገኘዉን የዓለም የሴቶች ቀን (ማርች 8ን) ምክንያት በማድረግ የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ያነጋገራቸዉ የትግራይ ተፈናቃይ ሴቶች እንደሚሉት ጦርነቱ  በተለይ በሴቶችና ህፃናት ላይ ያደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ ነዉ።ሴቶች እንደማንኛዉም ነዋሪ በጦርነቱ ከመጎዳታቸዉ በተጨማሪ  በሺዎች የሚቆጠሩ ተደፍረዋል፣ የተለያየ ፆታ ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋልም።

ትግራይ ዉስጥ ይደረግ በነበረዉ ጦርነት ከየቀያቸዉ የተፈናቀሉ የክልሉ ሴቶች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸዉን ይናገራሉ።ዛሬ በመከበር ላይ የሚገኘዉን የዓለም የሴቶች ቀን (ማርች 8ን) ምክንያት በማድረግ የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ያነጋገራቸዉ የትግራይ ተፈናቃይ ሴቶች እንደሚሉት ጦርነቱ  በተለይ በሴቶችና ህፃናት ላይ ያደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ ነዉ።ሴቶች እንደማንኛዉም ነዋሪ በጦርነቱ ከመጎዳታቸዉ በተጨማሪ  በሺዎች የሚቆጠሩ ተደፍረዋል፣ የተለያየ ፆታ ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋልም።
 

በመቐለ በሚገኙ የተለያዩ የተፈናቃዮች መጠልያ ጣብያዎች መታዘብ እንደሚቻለው በቁጥር የሚበዙ ተፈናቃዮች ሴቶች ናቸው። ዓለምአቀፉ የሴቶች ቀን አስመልክተን ያነጋገርናቸው በጦርነቱ ምክንያት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሴቶች በግዚያዊ መጠልያዎች የከፋ ሕይወት እየመሩ ስለመሆኑ ይገልፃሉ። 

የመቀሌ ተፈናቃዮች ማዕከልምስል Million Hailessilasse/DW

የሁለት ህፃናት እናት አመተ ብርሃነ ከጦርነቱ ጅማሮ በፊት በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ በአስተማሪነት ትሰራ የነበረች ናት። ከጦርነቱ ጅማሮ የመጀመርያ ሳምንታት ጀምሮ ፈታኝ ሕይወት ላይ መሆንዋ የምትገልፀው አመተ፥ ህፃናት ልጆችዋ እና በዕድሜ የገፉ እናትዋ ይዛ ከሶስት ግዜ በላይ ከቦታ ቦታ መፈናቀልዋ፣ አሁን ደግሞ ያለማንም ደጋፊ መቐለ በሚገኝ መጠልያ የከፋ ሕይወት እየመራች መሆኑ አውግታናለች። "ጦርነቱ ከሌላው በተለየ በሴቶች ሕይወት ላይ መጥፎ ሁኔታ ፈጥሯል" የምትለው አመተ ለራሷ ሳይሆን ለልጆችዋ የምታበላቸው አጥታ መጥፎ ቀናት ማሳለፍዋ፣ ይኽ ሕይወት አሁንም ሳይቀየር እየቀጠለ መሆኑ ነግራናለች። 

መቐለ በሚገኘው ቅሳነት ትምህርት ቤት የስደተኞች መጠልያ ጣብያ ያገኘናት የአምስት ህፃናት እናት አኸዛ ገብረሕይወት፥ መፈናቀል በተለይም ህፃናት ለያዙ ሴቶች ይበልጠ የከፋ  ስለሆኑ ታስረዳለች። በ2013 ዓመተምህረት ከሑመራ አካባቢ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀለቸው የአምስት ህፃናት እናት አኸዛ፣ ከህፃናት ልጆችዋ ጋር የከፋ ሕይወት እየገፋች ነው። አኸዛ "የምንተኛበት ምንጣፍ የለንም፣ ለህፃናት የምንሰጠው ምግብ የለንም፣ አስቸጋሪ ሕይወት እየመራን ነው" ትላለች። 

የቀድሞ አስተማሪዋ፣ አሁን ላይ ከቀዬዋ እና ስራዋ ተፈናቅላ ያለችው አመተ፥ ዛሬ እየተከበረ ያለው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክታ ስትናገር፣ በሴቶች ላይ የሚሰሩ ተቋማት በትግራይ ሴቶች ላይ የደረሰው በደል እንዲረዱ፣ ለመፍትሔ እንዲሰሩ፣ ፍትህ እንዲረጋገጥ ጥሪ ታቀርባለች። 

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዮማን ራይትስዎች ጨምሮ በርካታ ዓለምአቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በትግራዪ ጦርነት ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች መፈፀማቸው ሲገልፁ ቆይተዋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW