1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለወሰዱት ብድር የጦርነቱን ጊዜ ወለድ ክፈሉ የተባሉ የትግራይ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች አቤቱታ

ሐሙስ፣ የካቲት 28 2016

ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች በትግራይ ለሚገኙ ደምበኞቻቸው ከጦርነቱ በፊትላበደሩት ገንዘብ ባንኮች የጦርነቱን ጊዜ ጨምሮ ወለድ እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ለከፍተኛ ችግር እንዳጋልጣቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል። ያነጋገርናቸው በመቐለ በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የሚሰሩ ባለሐብቶች ሁሉም ባንኮች ብድራቸውን ከወለዱ ጋር እንዲከፍሉ እየጠየቋቁን ነው ብለዋል።

የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ
የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ ምስል Million Hailesilassie/DW

የጦርነቱን ጊዜ ወለድ ክፈሉ የተባሉ የትግራይ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች አቤቱታ

This browser does not support the audio element.

ጦርነቱ ተከትሎ በትግራይ ላይ የደረሰውን ውድመት ማጥናቱን የሚገልፀው የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር፥ አጠቃላይ የውድመቱ መጠን 80 ቢልዮን ዶላር መሆኑ በቅርቡ አስታውቋል። የሁለት ዓመቱ ጦርነት በትግራይ ባሉ የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንት ላይም ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል። የግል ባለሐብቶች ንብረት የሆኑ ኢንቨስትመንቶች ወድመዋል፣ ጥሬ ግብአቶች እና ማሽኖች እንዲሁ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፣ በባንኮች የነበረ ገንዘብ ለሁለት ዓመት አለመንቀሳቀሱ እና የዋጋ ንረቱ ተከትሎ ያስቀመጡት ገንዘብ የመግዛት አቅም መድከሙ ይገልፃሉ።በትግራይ ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት

በዚህ ብቻ አላበቃም በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ለሚገኙ ደምበኞቻቸው ላበደሩት ገንዘብ ባንኮች የጦርነቱን ጊዜ ጨምሮ ወለድ እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ለከፍተኛ ችግር እንዳጋልጣቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል። ያነጋገርናቸው በመቐለ በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የሚሰሩ ባለሐብቶች ሁሉም ባንኮች ብድራቸውን ከወለዱ ጋር እንዲከፍሉ እየጠየቋቸው መሆኑን ያነሳሉ። ፊልሞን አሰፋ ከጦርነቱ በፊት ከአንድ የግል ባንክ የወሰደውን ብድር፥ እየሰራ እየከፈለ እንደነበረ እና  ከአጠቃላይ ብድሩ እና የብድሩ ወለዱ ግማሹ ከፍሎ እንደነበር ይገልጻል። ይሁንና ከጦርነቱ መጀመር በኃላ ስራ በመቆሙ፣ ባንኮችም ለረዥም ግዜ ተዘግተው በመቆየታቸው ብድሩ የሚከፍልበት ዕድል አልነበረም። ነጋዴው ፊልሞን "ከጦርነቱ በፊት ከአጠቃላይ ብድሬ ግማሹ ከፍዬ ነበር። ይሁንና በጦርነቱ ግዜ መክፈል ባለመቻሌ፥ በተደራራቢ ወለድ ዳግም ወደ መጀመርያው ዕዳ ተመልሶ እንድከፍል ተጠይቄአለሁ" ይላል።

የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌምስል Million Hailesilassie/DW

ጦርነቱ በግል ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉ የሚገልፁት የትግራይ ንግድ እና ዘርፍ ማሕበራት ፕሬዝደንት አሰፋ ገብረስላሴ፥ ይህ እንዳለ ሆኖ ባንኮች በጦርነቱ ወቅት ተበዳሪዎችን ወለድ መጠየቃቸው ደግሞ የግሉን ዘርፉ ለከፍተኛ ችግር ዳርጎ ይገኛል ይላሉ። "የወደሙ፣ ወደ ዜሮ የተቀየሩ አሉ። ለዚህ ብድርህ ክፈል እየተባለ ነው። ሁለተኛ በከፊል የወደሙ አሉ። እነዚህ ጠግነው ወደ ስራ እንዳይገቡ መነሻ የለም። ከዛ ፍሪዝ የየተደረገው የባንክ ዕዳ፥ ብድር ክፈል ነው እየተጠየቀ ያለው" የሚሉት አቶ አሰፋ ገብረስላሴ ይህ ነጋዴዎችን ለአደጋ ዳርጎ እንዳለ ይገልፃሉ።የትግራይ ባንኮች ስራ መጀመር

በጦርነቱ ወቅት ሁሉም ባንኮች በትግራይ ስራ አቁመው የነበረ ቢሆንም አስቀድመው ላበደሩት ገንዘብ ግን ወለድ መጠየቃቸው ተገቢ አለመሆኑን ያነሳሉ በትግራይ ያሉ ነጋዴዎች። ይህ ቅሬታቸው ለተለያዩ ባንኮች፣ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች፣ ብሔራዊ ባንክ ብያስገቡም እስካሁን ምላሽ አለማግኘታቸው የትግራይ ንግድ እና ዘርፍ ማሕበራት ፕሬዝደንት አሰፋ ገብረስላሴ ይገልፃሉ።

በትግራይ የሚገኙ ነጋዴዎች እና ሌሎች ባለሐብቶች፥ መንግስት ችግሩ በማጤን የተለየ ውሳኔ በማስተላለፍ ወለድ እንዲያነሳላቸው፣ ተጨማሪ ድጋፍ ሊሰጣቸው ይጠብቃሉ። በዚህ ቅሬታ ዙርያ ከብሔራዊ ባንክ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW