1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች መልቀቃቸውን አስታወቁ

ዓርብ፣ ግንቦት 12 2014

በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት በቁጥጥሩ የነበሩ ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች እንዲለቀቁ መወሰኑ አስታወቀ። ዛሬ የተሸኙት 4 ሺሕ 208 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ዓውደ ውጊያዎች የተማረኩ እና እስከ 11 ወራት ድረስ በመቐለ የጦር ምርኮኞች ማዕከል የቆዩ ናቸው ተብሏል።

 Released Ethiopian National Defence Force ENDF Prisoners of War from Mekele center
ምስል DW

የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች መልቀቃቸውን አስታወቁ

This browser does not support the audio element.

በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት በቁጥጥሩ የነበሩ ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች እንዲለቀቁ መወሰኑ አስታወቀ። ዛሬ የተሸኙት 4 ሺሕ 208 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ዓውደ ውጊያዎች የተማረኩ እና እስከ 11 ወራት ድረስ በመቐለ የጦር ምርኮኞች ማዕከል የቆዩ ናቸው ተብሏል። የክልሉ መንግስት እንደሚለው ምርኮኞቹ ዛሬ በዓለም አቀፉ ቀይመስቀል ማሕበር ትብብር ከትግራይ ውጭ ይሸኛሉ። 

የተለየ ወንጀል መፈጸማቸው ከተረጋገጠባቸው እና ጉዳያቸው በሕግ ከሚታይ ውጪ ሌሎች በሺሕዎች የሚቆጠሩ የጦር ምርኮኞች በሒደት እንደሚለቀቁ የመቐለ የጦር ምርኮኞች ማዕከል አስተባባሪ አቶ ብርሀነ ከበደ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት አባል የሆኑ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ምርኮኛ ወታደሮች አሁንም በመቐለ የምርኮኞች ማዕከል እንደሚገኙ ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል። 

ዶይቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የመንግሥት የኮምዩንኬሽን አገልግሎት ባለሥልጣናትን አስተያየት ጠይቆ "መግለጫ እንሰጣለን" የሚል ምላሽ አግኝቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። 

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW