1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በትግራይ የህክምና መሳሪያዎች እጥረት አሳስቦኛል» አለም አቀፍ ቀይ መሰቀል ኮሚቴ

ዓርብ፣ ጥር 13 2014

የአለም አቀፉ ቀይ መሰቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጦርንቱን ተከተሎ በትግራይ የነበሩ የህክምና ተቋማት ወድመዋል።ከውደመት የተረፉትም በመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ሊሰሩ ወደማይችሉበት ደረጃ መወርዳቸውን አስታውቋል።በአማራና በአፋር ክልሎችም በጤና ተቋማት ላይ በደረሰ ውድመት ታማሚዎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውንም ገልጿል።

Logo Rotes Kreuz Roter Halbmond Roter Kristall
ምስል AP

በትግራይ የህክምና መሳሪያዎች እጥረት አሳስቦኛል አለም አቀፍ ቀይ መሰቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ

This browser does not support the audio element.

በትግራይ የህክምና ተቋማት በመውደማቸውና ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ዝግ በመሆናቸው ሆስፒታሎች በመድሃኒትና የህክምና መሳርያዎች እጥረት እየተቸገሩ መሆኑ አለምአቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አሳስቦኛል አለ።የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ለዶቸቨለ እንዳሉት ትግራይ ክልል የሚገኙ ሃኪም ቤቶች በህክምና ጓንት እጥረት ምክንያት አንዴ ብቻ ተጠቅመው መጣል የነበረባቸው ጓንቶች አጥበው ለመጠቀም እየተገደዱ ነው።በአማራና በአፋር ክልሎችም በጤና ተቋማት ላይ በደረሰ ውድመት ታማሚዎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውንም ቃል አቀባይዋ ገልጸዋል።

ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ሞት፣ ስደትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል።
ጦርንቱን ተከተሎ በትግራይ የነበሩ የህክምና ተቋማት ወድመዋል፣ ከውደመት የተረፉትም በመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ሊሰሩ ወደማይችሉበት ደረጃ መወርዳቸው እንዳሳሰበው የአለማቀፉ ቀይ መሰቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ፋጡማ ሳቶር ለዶቼቬለ DW ተናግራል።
            
«አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ይዞታ እጅጉን አሳስቦታል። በግጭቱ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በመፈናቅላቸው  በጤና ስርዓቱና የህክምና ባለሙያዎች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሯል። የመድሃኒትና የሀክምና መሳሪያዎች እጥረት በእጅጉ አሳስቦናል። የተወሰኑ የጤና ተቋማት ተጎድትዋል።  እነዚህ ሁሉ ችግሮች ሕዝቡ በተቋማቱ እንዳይጠቅም ችግሩን አወሳስበውታል።»

በትግራይ አሁንም የድርጅቱ ሠራተኞች እንዳሉ የገለጡት ፋጡማ ሳቶር ሠራተኞቻቸው በአካል ተመልክተው ስለሆስቲታሎቹ ችግሮቸ በምሳሌ ያስረዱትን እንዲህ ይገልጹታል
            

``በትግራይ ሃኪሞች አንዴ ብቻ ተጠቅመው መወገድ ያለባቸውን የህክምና ቁሳቁሶች በድጋሚ እየተጠቀሙባቸው ነው። ለምሳሌ ጓንቶች አጥበው የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው ያለው, የቀዶ ሀክምና መሳሪያዎች ፣ ሌላው ቢቀር ወደ በሽተኛው አፍ የሚገቡ የኦክስጅን መስጫ ቱቦዎች ደግምው እየተጠቀሙበት ይገኛል። ቁሰል የሚያጥቡበት ኬሚካል ስለሌላቸውም በትግራይ ሃኪሞች አንዴ ብቻ ተጠቅመው መወገድ ያለባቸውን የህክምና ቁሳቁሶች በድጋሚ እየተጠቀሙባቸው ነው።ቁሰል የሚያጥቡበት ኬሚካል ስለሌላቸውም ጨውን ለቁሰል ማጠቢያነት እየተጠቀሙ ነው።``በአማራና በአፋር ክልሎችም በጤና ተቋማት ላይ በደረሰ ውድመት ታማሚዎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውንም ቃል አቀባየዋ አክለዋል።
  
«በአማራ የመድሃኒት ችግር ያጋጠማቸው ወገኖቸ አሉን።  የደም ግፌት፣ HIVና የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ምንም እንኳ መደሃኒት በየቀኑ መወሰድ ቢጠበቅባቸወም የማግኘት ዕድሉ የላቸውም።  በዚህ ምክንያት በሽታቸው የሚወሳሰብባቸው እንዲያም ሲል የሚሞቱ አሉ። ጊዜ ያለፈበት መድሃኒት ለመጠቀም የሚገደዱበት ሁኔታም አለ።  ሆስቲታሎች ውሃና መብራት ስለሌላችው እናቶች በቤት ውስጥ ለመውለድ እየተገደዱ ነው።»

ድርጅታቸው በትግራይ፣ አማራ እና አፋር እንዲሁም በሌሎች ክልሎች የሰብአዊ እርዳታዎች እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ቃል አቀባይ ፋጡማ ሳቶር ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ዝግ በመሆናችው ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እንዳልቻሉ እና ይህ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ጋር ወይይት እየተደረገ እንደሆነ አክለዋል።

ዮሃንስ ግብረእግዚአብሄር

ሸዋዬ ለገሰ

  
 

 

 

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW