1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልላዊ ሐዘን ሦስተኛ ቀን

ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2016

ትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች የህልፈት መርዶ ለቤተሰቦች መነገሩ ተከትሎ ከፍተኛ ሐዘን ላይ ናት። በከተሞች እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል፣ በክልሉ ብሔራዊ ሐዘን ከታወጀ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። ለወትሮው በሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ፣ በግብይት እንዲሁም ሌሎች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ትደምቅ የነበረችው መቐለ ዛሬ እንደሁልጊዜው አይደለችም።

ፎቶ፤ ሀዘን የተቀመጡ ወገኖች በትግራይ
ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት የሞቱ ወገኖችን የተመለከተው ለሦስት ቀናት የቀዘለው ሀዘን በትግራይ። ፎቶ፤ ሀዘን የተቀመጡ ወገኖች በትግራይምስል Million Hailesilassie/DW

ትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች የህልፈት መርዶ ለቤተሰቦች መነገሩ ተከትሎ ከፍተኛ ሐዘን ላይ ናት። በከተሞች እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል፣ በክልሉ ብሔራዊ ሐዘን ከታወጀ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል።

ለወትሮው ሁሌም ሰኞ ዕለት ከጠዋት ጀምሮ በሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ፣ በግብይት እንዲሁም ሌሎች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ትደምቅ የነበረችው መቐለ ዛሬ እንደሁልጊዜው አይደለችም። በመቐለ ጎዳናዎች ከሌላው ግዜ በተለየ ብዛት፥ ዛሬ ላይ የሚስተዋለው ወደ ለቅሶ ቤት የሚሄድ እና የሚመለስ ሐዘንተኛ፣ ነጠላ የዘቀዘቁ እንስቶች፣ ጥቁር የለበሱ ወጣቶች፣ በሐዘን የተጎሳቆሉ እናቶች እና አባቶች ናቸው።ትግራይ ክልል መርዶ መንገሩ ቀጥሏል ልክ እንደመቐለ ሌሎች የትግራይ ከተሞቻ እና የገጠር አካባቢዎች እንዲሁ በከባድ የሐዘን ድባብ ላይ ናቸው። ከማይጨው፣ ዓዲግራት፣ ሽረ፣ አክሱም እና ሌሎች ከተሞች ያነጋገርናቸው የየከተማው ነዋሪዎች ካለፉት ግዜያት፣ በተለይም ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከተለመደ ሁኔታቸው ርቀው በሐዘን ላይ መሆናቸው እንደሚታይ ገልፀውልናል። በአጠቃላይ ከቅዳሜ ጀምሮ ብሔራዊ ሐዘን በታወጀባት ትግራይ፥ በተለያዩ የጦር ግንባሮች ያለፉ የቀድሞ ተዋጊዎች መርዶ ለቤተሰቦቻቸው ተነግሮ ከፍተኛ የሐዘንን ፀጥታ ድባብ ሰፍኖባት ይገኛል። በመቐለ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ፥ የቅርብ ቤተሰባቸው፣ አብሮአደጎቻቸው፣ ወንድም እህታቸው ማጣታቸው ገልፀው ከባድ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ያስረዳሉ። አስተያየቱ የሰጠን ወጣት አማኑኤል ሃይለ "ትግራይ ሐዘን ላይ ናት።በትግራይ የ3 ቀናት ክልላዊ ሃዘን ታወጀ ትልቁ ትንሹ፣ ወንዱ ሴቱ ሁሉም። ሁሉም ነጠላ ለብሶ፣ እያለቀሰ ነው የምታየው። እኔ በርካታ አብሮ አደጎቼ፣ የሰፈሬ ልጆች፣ አብረውኝ የተማሩ አጥቻለሁ። የትኛው ሀዘን ደርሰህ የትኛው መተው እንዳለብህ እስኪጠፋብህ ድረስ በአንድ ግዜ መርዶው መጥቷል። እንደዚህ ዓይነት ፈታኝ ግዜ የለም። ለቅሶ በመድረስ ደከምን። አሁን እኔ ዕዳጋዓርቢ ሄጄ የዘመድ ለቅሶ መድረስ ነበረብኝ። ግን እዚህ ያሉትስ ብዬ ተውኩት። ለትግራይ ህዝብ መፅናናትን ነው የምመኘው" ይላል።

ለወትሮው ሁሌም ሰኞ ዕለት ከጠዋት ጀምሮ በሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ፣ በግብይት እንዲሁም ሌሎች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ትደምቅ የነበረችው መቐለ ዛሬ እንደሁልጊዜው አይደለችም። በመቐለ ጎዳናዎች ከሌላው ግዜ በተለየ ብዛት፥ ዛሬ ላይ የሚስተዋለው ወደ ለቅሶ ቤት የሚሄድ እና የሚመለስ ሐዘንተኛ፣ ነጠላ የዘቀዘቁ እንስቶች፣ ጥቁር የለበሱ ወጣቶች፣ በሐዘን የተጎሳቆሉ እናቶች እና አባቶች ናቸው።ምስል Million Hailesilassie/DW

ሌላው አስተያየት ሰጪ ዳኒኤል መብራህቱ "በርካታ ጓደኞቻችን፣ የዕድሜ እኩዮቻችን፣ በርካቶች አጥተናል። አሳዛዥ ድባብ ነው ያለው። እናቶች ልጆቻቸው አጥተው ሲያለቅሱ እንደማየት የሚያም ነገር የለም። ብዙ ብርቅዬ ወንድሞቻችን አጥተናል። ለእኛ ሲሉ ነው ይህ ሁሉ የሆኑት። ሰማእታት ናቸው። ትግራይ በየግዜው በርካቶች እየገበረች መኖር የለባትም። ያለፈው ይበቃል። ከእኛ ጀምሮ፥ ይህ እንዳይደገም ጥረት ይፈልጋል" ብሏል።

በመቐለ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ፥ የቅርብ ቤተሰባቸው፣ አብሮአደጎቻቸው፣ ወንድም እህታቸው ማጣታቸው ገልፀው ከባድ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ያስረዳሉ። አስተያየቱ የሰጠን ወጣት አማኑኤል ሃይለ "ትግራይ ሐዘን ላይ ናት።ምስል Million Hailesilassie/DW

ከመቐለ ውጪም፥ በውቅሮ እና አካባቢው ያለው ሁኔታ የገለፁልን አቶ ብርሃነ ወልደአበእዝጊ ትግራይ ተስፋ ይሆንዋት የነበሩ ምሁራን፣ ወጣቶች አጣች ይላሉ። ብርሃነ "እንኳን ለወለደ ለማንም ፍጡርም የሚያስለቅስ ነው። በእኛ አከባቢ በመቶዎች የሚቆጠር ቤተሰብ ነው መርዶ የደረሰው።የትግራይ ክልል በሁለቱ ዓመት ጦርነት የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ቤተሰቦችን በይፋ ማርዳት ተጀመረ በዚህ ሶስት ቀን ብቻ ሳይሆን፣ ከአሸንዳ ሰሞን ጀምሮ እስካሁን ነው ሐዘኑ ያለው። የተማሩ ልጆች፣ ሐኪሞች፣ ኢንጅነሮች፣ ባለሙያዎች አጥተናል። ደሞም ሮጠው ያልጠገቡ ታዳጊዎች፣ ተስፋ የምንላቸው የነበረ ወጣቶች ናቸው ያለቁት። በየቤተክርስቲያኑ ከአስር፣ ከሀያ በላይ መርዶ ነው የምትሰማው። በጣም አስቸጋሪ ነው" ሲል ገልጿል።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ዳኒኤል መብራህቱ "በርካታ ጓደኞቻችን፣ የዕድሜ እኩዮቻችን፣ በርካቶች አጥተናል። አሳዛዥ ድባብ ነው ያለው። እናቶች ልጆቻቸው አጥተው ሲያለቅሱ እንደማየት የሚያም ነገር የለም። ብዙ ብርቅዬ ወንድሞቻችን አጥተናል። ለእኛ ሲሉ ነው ይህ ሁሉ የሆኑት። ሰማእታት ናቸው። ትግራይ በየግዜው በርካቶች እየገበረች መኖር የለባትም። ያለፈው ይበቃል። ከእኛ ጀምሮ፥ ይህ እንዳይደገም ጥረት ይፈልጋል" ብሏል።ምስል Million Hailesilassie/DW

ለሁለት ዓመት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የትግራይ ሐይሎች መካከል የተደረገው ጦርነት በተለይም በሰው ሕይወት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱ ይገለፃል። በትግራይ ሐይሎች በኩል በውግያ ግንባሮች ያለፉት ቁጥር ስንት መሆኑ እስካሁን በክልሉ አስተዳደር በግልፅ ባይቀመጥም፣ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ሰጥተውት በነበረ መግለጫ "ከፍተኛ ኪሳራ" መድረሱ ጠቁመው ነበር።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW