1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል መንግስት ምርጫው መካሄድ አለበት አለ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2012

የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ሐላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ ሆና ጭምር ምርጫ የማካሄድ ልምድ ነበራት ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፌደራሉ መንግስት ሀገራዊ ምርጫ የማያካሂድ ከሆነ የትግራይ ክልል መንግስት ለምርጫ ዝግጅት ማድረግ አለበት ብለዋል።

Äthiopien Mekelle | Öffentlichkeitsarbeit | Lia Kassa
ምስል DW/M. Haileselassie

በመጪው ምርጫ ላይ የትግራይ ክልል መንግስት አቋም

This browser does not support the audio element.

የትግራይ ክልል መንግስት ዘንድሮ ሊካሄድ እቅድ ወጥቶለት የነበረው ሀገራዊ ምርጫ በወቅቱ መካሄድ ይገባዋል ሲል ገለጿል፡፡ የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ሐላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ ሆና ጭምር ምርጫ የማካሄድ ልምድ ነበራት ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፌደራሉ መንግስት ሀገራዊ ምርጫ የማያካሂድ ከሆነ የትግራይ ክልል መንግስት ለምርጫ ዝግጅት ማድረግ አለበት ሲሉ ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ወቅታዊው የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ የምርጫ ዝግጅቱ መግታቱ ይገልፃል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ታምራት ዲንሳ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW