1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራይ ገበሬዎች ሮሮ

ሐሙስ፣ ሰኔ 29 2015

ከጦርነቱ መቆም 8 ወራት በኃላም ቢሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች እና ቤተሰቦቻቸው አሁንም ወደ ማሳቸው ብሎም ወደ ቀዬአቸው ሳይመለሱ የክረምት ወቅት መድረሱ፣ በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ሊቀጥል ዕድል የሚፈጥር ተብሏል።

Äthiopien | Landwirtschaft in Tigray
ምስል፦ Million Haieselassie

ዘንድሮ ካልታረሰ ለመጪዉ ዓመትም ችግር ነዉ-ገበሬ

This browser does not support the audio element.

ትግራይ ዉስጥ ይደረግ የነበረዉ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከቆመ 8 ወራት ቢያስቆጥርም በጦርነቱ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ገበሬዎች አሁንም ወደየቀያቸዉ ባለመመለሳቸዉ ማረስ አልቻሉም።ወደ የቀያቸዉ የተመለሱትና ወትሮም ያልተፈናቀሉት ገበሬዎች ደግሞ በማደበሪያና በምርጥ ዘር እጥረት ምክንያት ለማረስ መቸገራቸዉን እየተናገሩ ነዉ።ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከ75 ከመቶ የሚበልጠዉ የትግራይ ሕዝብ ገበሬ ነዉ።

ከጦርነቱ መቆም 8 ወራት በኃላም ቢሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች እና ቤተሰቦቻቸው አሁንም ወደ ማሳቸው ብሎም ወደ ቀዬአቸው ሳይመለሱ የክረምት ወቅት መድረሱ፣ በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ሊቀጥል ዕድል የሚፈጥር ተብሏል። 

አርሶአደር ወልዳይ ገብረእግዚአብሔር - ከምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ ተፈናቅለው አሁን በሽረ መጠልያ ያሉ ናቸው። ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው ማረስ አለመቻላቸው፥ ያለባቸው ችግር እንዳወሳሰበው እንዲሁም መጪው ዓመት ደግሞ እንደሚያሰጋቸው ይናገራሉ። አርሶአደሩ "ወደ ቀዬአችን እንመለሳለን፣ ማሳችን እናርሳለን የሚል ተስፋችን አሁን ላይ ተሟጧል። የልመና ኑሮ መሮናል፣ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም" ይላሉ።

የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት፣ የዋጋ ውድነት፣ የአንበጣ እና ሌሎች ተምቾች ስጋት የግብርና ስራቸው ላይ አደጋ ደቅነዋል። ያነጋገርናቸው አርሶአደር ተክለሃይማኖት አብርሃ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የክልተ አውላዕሎ ነዋሪ ናቸው። የማዳበርያ ውድነት እንዲሁም የአቅርቦት ውሱንነት አሳሳቢ መሆኑ ገልፀውልናል። አርሶአደር ተክለሃይማኖት "ከጦርነቱ በፊት የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ 2800 ብር ነበረ። አሁን 6000 ብር ገብቷል። ከመወደዱ በላይ በቂ አቅርቦት የለም። ስንጠይቃቸው አልመጣልንም ነው የሚሉት" ይላሉ።

እንደ የትግራይ ግብርና ቢሮ መረጃ በዘንድሮው የምርት ዘመን በክልሉ 23 ሚልዮን ኩንታል የግብርና ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ዕቅድ የወጣ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ተፈፃሚነቱ አጠራጣሪ ሆንዋል። የትግራይ ግብርና ቢሮ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ "ከፍተኛ የግብርና ግብአቶች እጥረት" መኖሩ ያብራራሉ። 

እንደ ቢሮው መረጃ በክልሉ ለሚከወን የክረምት ወቅት የግብርና ስራ 800 ሺህ ኩንታል ማዳበርያ የሚያስፈልግ ቢሆንም እስካሁን ወደ ትግራይ የገባው ከ20 በመቶ በታች ነው። የምርጥ ዘር አቅርቦት በሚመለከት ለክልሉ ከሚያስፈልገው 370 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር እስካሁን የተገኘው ከ10 በመቶ አይዘልም። ይህ የአቅርቦት ውሱንነት ከሌሎች ወቅታዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ በትግራይ የግብርና ስራው አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል።

የማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር እና ሌሎች የግብርና ግብአቶች እጥረት በትግራይ የግብርና ዘርፉ እየፈተኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ በርካታ አርሶአደሮች አሁንም ወደ ቀዬአቸው ባለመመለሳቸው ማረስ አልቻሉም። 

አቶ ሚካኤል ምሩፅ የትግራይ ግብርና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊምስል፦ Million Haieselassie

ከ75 በመቶ በላይ በቀጥታ በግብርና ስራ የሚተዳደር ህዝብ ባለባት ትግራይ የዘንድሮው የክረምት የግብርና ወቅት በፈተናዎች የታጀበ ሆንዋል። ከጦርነቱ መቆም 8 ወራት በኃላም ቢሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች እና ቤተሰቦቻቸው አሁንም ወደ ማሳቸው ብሎም ወደ ቀዬአቸው ሳይመለሱ የክረምት ወቅት መድረሱ፣ በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ሊቀጥል ዕድል የሚፈጥር ተብሏል። 

አርሶአደር ወልዳይ ገብረእግዚአብሔር - ከምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ ተፈናቅለው አሁን በሽረ መጠልያ ያሉ ናቸው። ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው ማረስ አለመቻላቸው፥ ያለባቸው ችግር እንዳወሳሰበው እንዲሁም መጪው ዓመት ደግሞ እንደሚያሰጋቸው ይናገራሉ። አርሶአደሩ "ወደ ቀዬአችን እንመለሳለን፣ ማሳችን እናርሳለን የሚል ተስፋችን አሁን ላይ ተሟጧል። የልመና ኑሮ መሮናል፣ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም" ይላሉ።

በደህናው ግዜ ጥረው ግረው ይበሉ የነበሩ እንደ ወልዳይ የመሰሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች አሁን ከማሳቸው ርቀው፣ ይመጣል የሚባል የእርዳታ ስንዴ ጠባቂ ሆነዋል። ከጦርነቱ አሰቃቂ ጥፋት የተረፉ እና በማሳቸው የሚገኙ የትግራይ አርሶአደሮችም ቢሆን የክረምቱ የግብርና ስራ ፈታኝ ሆኖባቸዋል። የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት፣ የዋጋ ውድነት፣ የአንበጣ እና ሌሎች ተምቾች ስጋት የግብርና ስራቸው ላይ አደጋ ደቅነዋል። ያነጋገርናቸው አርሶአደር ተክለሃይማኖት አብርሃ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የክልተ አውላዕሎ ነዋሪ ናቸው። የማዳበርያ ውድነት እንዲሁም የአቅርቦት ውሱንነት አሳሳቢ መሆኑ ገልፀውልናል። አርሶአደር ተክለሃይማኖት "ከጦርነቱ በፊት የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ 2800 ብር ነበረ። አሁን 6000 ብር ገብቷል። ከመወደዱ በላይ በቂ አቅርቦት የለም። ስንጠይቃቸው አልመጣልንም ነው የሚሉት" ይላሉ።

እንደ የትግራይ ግብርና ቢሮ መረጃ በዘንድሮው የምርት ዘመን በክልሉ 23 ሚልዮን ኩንታል የግብርና ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ዕቅድ የወጣ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ተፈፃሚነቱ አጠራጣሪ ሆንዋል። የትግራይ ግብርና ቢሮ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሚኪኤለ ምሩፅ "ከፍተኛ የግብርና ግብአቶች እጥረት" መኖሩ ያብራራሉ። 

እንደ ቢሮው መረጃ በክልሉ ለሚከወን የክረምት ወቅት የግብርና ስራ 800 ሺህ ኩንታል ማዳበርያ የሚያስፈልግ ቢሆንም እስካሁን ወደ ትግራይ የገባው ከ20 በመቶ በታች ነው። የምርጥ ዘር አቅርቦት በሚመለከት ለክልሉ ከሚያስፈልገው 370 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር እስካሁን የተገኘው ከ10 በመቶ አይዘልም። ይህ የአቅርቦት ውሱንነት ከሌሎች ወቅታዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ በትግራይ የግብርና ስራው አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW