የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ጋዜጣዊ መግለጫ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 2016ዛሬ ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ማብራሪያ የሰጡት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት እና የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ወቅታዊ የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ሂደት ላይ ያለው ተፈናቃዮች ለመመለስ የሚደረግ ጥረት ዳሰዋል። በትግራይ ፖለቲካዊ ውጥረት መንገሱ ያነሱት ጀነራል ታደሰ ወረደ ይህ ፖለቲካዊ አለመግባባት ወደተለየ ሁኔታ እንዳይሰጋገር ወይም የሰላምና ፀጥታ ችግር እንዳይፈጥር፥ የሚመሩት ኃይል በገለልተኝነት እና በጥንቃቄ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል። ጀነራል ታደሰ የትግራይ ኃይሎች የማንም ወገን ደጋፊ ሳይሆኑ ገለልተኛ ሆነው እንደሚቀጥሉ ያነሱ ሲሆን በትግራይ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ግን የውጭ ኃይል ተፅእኖ ይሁን እጅ ማስገባት ተቀባይነት እንደማይኖረው አንስተዋል።
ጀነራል ታደሰ "የትግራይ ፖለቲካ ችግሮች ሊፈጠሩበት ይችላል፣ ፈፅሞ ግን መውደቅ የለበትም። ይህ እንዳይሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠር መቻል አለበት። የትግራይ ፖለቲካ ዘዋሪ እዚህ ትግራይ ውስጥ መሆን አለበት። የውጭ ዘዋሪ አያስፈልገውም። የውጭ ጫና ያነሰ ማድረግ እና ዋናው ጉዳይ ተጋሩ ተዋናዮች መሆን አለባቸው። ይህ እንዲሆን የተቻለው ሁሉ እናደርጋለን። የተለያየ የፖለቲካ አቋም ያለውም ይህ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለበት" ብለዋል።
ትግራይ ክልል እየተፈፀሙ ናቸው በተባሉ ወንጀሎች ላይ ዘመቻ መከፈቱ
ከዚህ በተጨማሪ በሂደት ላይ ያለው የጦርነቱ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው የመመለስ ጥረት ያነሱት ጀነራል ታደሰ ወረዳ፥ ቀሪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደቤታቸው ለመመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ በተጨማሪ የተመለሱት ተፈናቃዮች ላይ ከተለያዩ አካላት ጨናዎች መኖራቸው ጠቁመዋል። ይህ በተመላሾች ላይ እየደረሰ ነው ያሉት ችግሮች ለመፍታት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑ አስታውቀዋል።
ጀነራሩ "በተመላሾች ላይ ተፅእኖ እየተፈጠረ ነው። ይህ ለሚመለከተው አስታውቀናል። ሰብአዊ ድጋፍም ቢሆን ተፈናቃዮ ወደተመለሰበት ቦታ እንዲደርስ አስታውቀናል። ተመላሹን እንዳይረጋጋ የሚሰራ ስራ አለ። ይህ መከላከያ ከወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የግድ ሊፈታው ይገባል" ብለዋል።
ግዚያዊ አስተዳደሩ ጀመረው የተባለ በትግራይ በማእድናት ምዝበራ፣ ብረታብረት ዝርፍያ እና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ አካላት እየለዩ ለሕግ ማቅረብ እንደሚቀጥልም ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ልደት አበበ
ዮሃንስ ገብረእግዚዓብሄር