1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቺሊው ርዕደ መሬት ያስከተለው ጉዳት

ሰኞ፣ የካቲት 22 2002

ባለፈው ቅዳሜ ቺሊን በመታው በሬክተር ስኬል 8.8 በተለካ ርዕደ መሬት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከሰባት መቶ በላይ መሆኑን መንግስት አስታውቋል ።

ምስል፦ AP
የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችልም ተገምቷል ። አደጋው የከፋ ጉዳት ባስከተለባት ኮንሴፕስዮን በተባለችው ከተማ የተከሰተውን ዝርፊያና ሁከት ለማስቆምም ትናንት ከምሽት እስከ ንጋት ሰዓት ዕላፊ ቢጣልም ነዋሪዎች አሁንም ከዝርፊያው ስጋት አልተላቀቁም ። በርካታ የአደጋው ሰለባዎች ዕርዳታ አልደረሰንም ሲሉ በማማረር ላይ ናቸው ። የዶይቼቬለው ሽታይን ጎትፍሪድ ከቦነስ አይሪስ የላከውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW