1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይናው ፕሬዚደንት የሞስኮ ጉብኝት እና አንድምታው

ረቡዕ፣ መጋቢት 13 2015

የቻይናው ፕሬዝደንት ጂፒንግ በሞስኮ ያደረጉትን የ2 ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አገራችው ተመልሰዋል። ፕሬዝድንት ጂፒንግ ወደ ሞስኮ ያቀኑት ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ፑቲን ባቀረቡላቸው ግብዣ ሲሆን፤ ሁለቱ መሪዎች ባደረጓቸው ውይይቶችም በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች በጋራ ለመስራትና ወዳጅነታቸውን ለማጠናከር የተስማማሙ መሆኑ ተገልጿል።

Russlands Putin führt Gespräche mit Chinas Xi in Moskau
ምስል Sputnik/Mikhail Tereshchenko/Pool via REUTERS

የፕሬዚደንት ሺ ዢንፒንግ የሞስኮ ጉብኝት መጠናቀቅ

This browser does not support the audio element.

የቻይናው ፕሬዝደንት ጂፒንግ በሞስኮ ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደአገራችው ተመልሰዋል።  ፕሬዝድንት ጂፒንግ ወደ ሞስኮ ያቀኑት ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ፑቲን ባቀረቡላቸው ግብዣ ሲሆን፤ ሁለቱ መሪዎች ባደረጓቸው ውይይቶችም በሁለትዮሽና ዓለማቀፍ ጉዳዮች በጋራ ለመስራትና ወዳጅነታቸውን ለማጠናከር የተስማማሙ መሆኑ ተገልጿል። 

የፕሬዝዳንት ጂፒንግ ጉብኝት በተለይ ምራባውያን በዩክሬን ጦርነት ምክኒይት ከሩሲያ ጋር በቀጥታም ባይሆን በኢኮኖሚና ፖለቲካው በክፍተኛ ጦርነት ውስጥ በሚገኙበትና ፕሬዝዳንት ፑቲንም ባለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል በሚባልበት ወቅት በመሆኑ፤  የሁሉንም ትኩረት የሳበ ሁኗል። ከሁሉም በላይ ግን ጉብኝቱ ሩሲያ ምራባውያን እንዳሰቡት የተገለለችና ባይታወር ሆና የቆመች አለመሆኑን ያረጋገጠችበት ነው ተብሏል። 

ምስል Sputnik/Mikhail Tereshchenko/Pool via REUTERS

በጉብኝቱ ወቅት ሁልቱ መሪዎች ያስዩዋቸው ወዳጅነቶችና ያደርጓቸው ንግግሮች ከተፈረሙት የትብብር ስነዶች የበለጠ የሁለቱን አገሮች የግንኑነት ደረጃ የሚገልጹ ሆነው ታይተዋል።  ፕሬዝደንት ጂፒንግ “ ወዳጀ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያቀረብክልኝን የጉብኝት ግብዣ በደስታ ነው የተቀበልኩት። የኮሚኒስት ፓርቲው ሊቀመንበር ሆኘ ዳግም እንደተመረጥኩም ሩሲያን የመጀመሪያው የውጭ ጉብኝት መዳረሻየ ነው ያደረኩት በማለት ለሳቸውና ለሩሲያ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲንም እንደዚሁ ቻይናና መሪዋ ጂፒንግ ለሩሲያ የክፉ ቀን የልብ ወዳጅ መሆናቸውን  በመግለጽ ግንኑነታቸው ረጅም ታሪክ ያለውና ጥልቅ መሆኑንም ገልጸውላቸዋዋል። 

ሁለቱ መሪዎች በመጨረሻ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ወዳጅነታቸውንና ትብብራቸውን ለማጠናከር ከመግለጽ በተጨማሪ፤ ምራባውያን በተለይም አሜርካ፤ የዓለምቀፉን ስራት በማናጋት ላይ መሆናቸውንና  የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ  ወደ እስያና ፓስፊክ  አካባቢዎች ጭምር የሚያማትር መሆኑን በመጥቀስ አውግዘዋል።  ቻይና ቀደም ሲል የሩሲያንና ዩክሬንን ጦርነት በውይይት ለማስቆም የሚያስችል የሰላም ዕቅድ ማቅረቧ የሚታወስ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን በሰላም እቅዱ የቀረቡት ብዙዎቹ ሀስቦች ከሩሲያ ዓቋም ጋር የሚገናኙ መሆኑን በመጥቀስ፤  ከኪየቭና ምራባውያን ፈቃደኝነት ካለ፤ የቀረቡትን ሀሳቦች ለውይይት መነሻ ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጠውላቸዋል።ቻይና የዩክሬንን የግዛት አንድነትና ልኡላዊነት እውቅና የምትሰጥ ሲሆን፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ግን እስካሁን አላወገዘችም። ለጦርነቱ መቀስቀስም ሆነ መባባስ ምራባውያንን በተለይም ኔቶን ተወቃሽ የምታደርገው  ቻይና፤ ባቀረበችው የሰላም ዕቅድ ምዕራባውያን የጦር መሳሪያ  ለዩክሬን በገፍ በማቀበልና በሩሲያ ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር  ጦርነቱን እንዲራዘም ከማድረግ እንዲቆጠቡና ሁለቱ ወገኖች ግን ተኩስ በማቆም ችግሮቻቸውን በውውይት እንዲፈቱ ጠይቃለች።  

ኪየቭ ሀሳቡን በጥንቃቄ እያየቸው እንደሆነና የቻይናው መሪም ከፕሬዝዳንት ዘለንሲኪ ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተለጸ ቢሆን፤ የጦርነቱ ዘዋሪዎች ናቸው የሚባሉት አሜሪካና ምራባውያን ግን የቻይናው መሪ ጉብኘት በራሱ የቻይናን ገለልተኘነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን በመጥቀስ የሰላም ሀስቡና የተኩስ ማቆም ጥሪው ተቀባየነት ሊኖረው እንደማይችል ነው የሚገልጹት።የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር  ሚስተር አንቶኒ ቢሊንከን በዚህ ጉዳይ በሰጡት አስተያየት፤ “ የሩሲያን ወታደሮች ከኪየቭ ግዛት መውጣትን የማይጠይቅ የትኩስ አቁም ጥሪ፤ ሩሲያ በዩክሬን ግዛት ላይ ያደረገችውን ወረራ የሚይጸድቅ ነው የሚሆነው በማለት የሰላም ዕቅዱ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይችል ገልጸዋል። 

ምስል SERGEI KARPUKHIN/AFP

የኔቶ ዋና ጸሀፊ ሚስተር ስቶልቴንበርግ በበኩላቸው፤ “ ማንኛውም የዩክሬንን የግዛት አንድነትና  ሉአላዊነትን የማያከብር የተኩስ ማቆም ስምምነት፤ ሩሲያ እንደገና ተጠናክራ ጦርነቱን እንድትቀጥል ጊዜ የሚሰጥ እንጂ፤  ሰላም ሊያመጣ የሚችል አይሆንም በማለት ሀሳቡን አጣጥለውታል ። 

ቻይና ግን የሰላም ሀሳቡን እንደምትገፋበት የሜጠቅ ሲሆን፤ በቅርቡ በኢራንና ሳኡዲ አረቢያ መካከል ያልተጠበቀ እርቅ እንዳወረደች ሁሉ፤ ይህንን አስከፊ ጦርነት ለማስቆምም የሞራል ልእልና ያላት ብቸኛ አገር እሷው ናት በማለት ተስፋ የሚያደርጉ ጥቂቶች እንዳልሆኑ ነው የሚነገረው።  

ጉብኝቱ ግን ባጠቃላይ፤ ቻይናና ሩሲያ ከምራባውያን አንጻር በአንድነት የቆሙ ሀይሎች መሆናቸውንና  ሩሲያም ከምራባውያን የተጣለባትን ማዕቀብ ክቻይና ጋር በምታደርገው መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ግንኑነት የምትቁቋመው መሆኑን ያሳየችበት ሆኖ ታይቷል።

ገበያው ንጉሤ 

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW