1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቻዴማ ፓርቲ ከምርጫ መታገድ እና የታንዛንያ ዴሞክራሲ መንሸራተት

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11 2017

የታንዛንያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር በሚደረገው አጠቃላይ ምርቻ እንዳይሳተፍ አግዷል። ለፓርቲው ከምርጫ ውድድሩ መታገድ የምርጫ የስነ ምግባር ደንቡን ተቀብሎ አለመፈረሙ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

Tansania Daressalam 2024 | Führung der Oppositionspartei CHADEMA bei Treffen
ምስል፦ Eric Boniface/DW

የተቃዋሚ ፓርቲ ከምርጫ መታገድ እና ስጋት የተጋረጠበት የታንዛንያ ዴሞክራሲ

This browser does not support the audio element.

የታንዛንያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር በሚደረገው አጠቃላይ ምርቻ እንዳይሳተፍ አግዷል። ለፓርቲው ከምርጫ ውድድሩ መታገድ የምርጫ የስነ ምግባር ደንቡን ተቀብሎ አለመፈረሙ በምክንያትነት ተጠቅሷል። 
የምርጫ ኮሚሽኑ ዕገዳ እንደተሰማ የታንዛንያን ዴሞክራሲ ወዴት እያመራ ይሆን የሚል ጥያቄ በበርካቶች  እንዲነሳ አድርጓል። 
እገዳውን ተከትሎ ፓርቲው እስከ ጎርጎርሳዉያኑ 2030 ድረስ ታንዛንያ ውስጥ በሚደረጉ ማንኛዉም ምርጫ ላይ የመሳተፍ ዕድል እንደማይኖረው ነው የተገለጸው ። 
ቻዴማ የምርጫ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ እና ህጉን ያልተከተለ ነው ሲል ተቃዉሞውን አሰምቷል። 
ይህንኑ በተመለከተ የቻዴማ ፓርቲ ዐቃቤ ሕግ ሬሜሌዛ ንሽላ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት በፓርቲው ላይ የቀረበው ውንጀላ እና የተላለፈው ዉሳኔ ለታንዛንያዉያን እና ለቻዴማ ፓርቲ የስድብ ያህል ነው። 
የፓርቲው መሪ ቱንዱ ሊሱ ቀደም ሲል በሀገሪቱ የምርጫ ማሻሻያ መጠየቃቸውን ተከትሎ በሀገር ክህደት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።
በጎርጎርሳዊዉ 2017 ከጥይት እርምታ ያመለጡት ፖለቲከኛው አሁን ከበድ ያለ እስር ሳይገጥማቸው እንደማይቀር ነው አየተነገር  ያለው ። 

ሴቶች በአፍሪቃ የተሻለ የፖለቲካ ውክልና አላቸውን ?

የታንዛንያ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን መስመር ተላልፎ ይሆን? የሚል ጥያቄ ይነሳበታል። 
የፖለቲካ ተንታኙ ፓተርነስ ኒዬጋራ ከቻዴማ ዉሳኔ ጋር ይስማማሉ። አንድ ፓርቲ የምርጫ ህጉን ካልፈረመ ህጉ ለቅጣት በተቀመጡት ድንጋጌዎች ላይ ግልፅ አለመሆኑን  የሚያሳይ ነው ሲሉ ለDW ተናግረዋል።
"የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ግለሰብ የስነ-ምግባር ደንቡን ካልፈረመ ይህን እንዳያደርግ  የሚከለክለው ህግ አሁንም ግልጽ አይደለም። ክልከላ የሚጥሉ  አንቀጾቹ አሁንም አከራካሪ ናቸው ። እገዳውን ለመቃወም ክፍት ነው"
እንደተባለው የቻዴማ ፓርቲ በሀገሪቱ የምርጫ ስረዓት ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ አጥብቆ ይፈልጋል። 
ምክንያቱ ደግሞ ኮሚሽኑ ከገለልተኝነቱ ይልቅ ለገዢው የቻማ ቻ ማፒንዱዚ ፓርቲ ይወግናል የሚል ነው። 
በጎርጎርሳዊው  2024 በተደረገው የአካባቢ አስተዳደር ምርጫ ለደረሰው ከባድ ኪሳራ  የኮሚሽኑ አድሏዊ የሆኑ የምርጫ ህጎች እና ጭቆናን  በምክንያት የሚያነሳው ፓርቲው በእነዚያ የአካባቢ ምርጫዎች ገዢው ፓርቲ ከ98% በላይ መቀመጫዎችን እንዲያሸንፍ አድርጓል ሲል ይከሳል።

የፓርቲው መሪ ቱንዱ ሊሱ ቀደም ሲል በሀገሪቱ የምርጫ ማሻሻያ መጠየቃቸውን ተከትሎ በሀገር ክህደት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉምስል፦ Emmanuel Herman/REUTERS

የታንዛንያ የአካባቢ ምርጫዎች ውጤትና ፕሬዝዳንት ሳሚያ

በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት የተደረገው የአካባቢ አስተዳደር ምርጫ የታንዛኒያ የዲሞክራሲ ተቋማት ፈተና መሆኑ ታይቷል። በጎርጎርሳዉያኑ 1964 የታንጋኒካ እና የዛንዚባርን ውህደት ተከትሎ ታንዛኒያ የተባበረ ሪፐብሊክ ከሆነች በኋላ ገዢው የCCM ፓርቲ የፖለቲካ የበላይነት ይዞ መቆየቱን ነው ንሻላ የሚናገሩት።
"እየተፈጠረ ያለ አስከፊ ነገር አለ። እገዳው በምርጫ ኮሚሽኑ በኩል የተሰላ እርምጃ ነው። ቻዴማ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫን ያልተከተለ ኮድ እንዲፈርም ለማስገደድ ያለመ ነው። ይህንን እንቃወማለን"
የቻዴማ ፓርቲ መሪ ምንም እንኳ መሪው በእስር ላይ ቢገኝም ፤ ምንም እንኳ ፓርቲው ከቀ,ጣዩ ምርጫ ቢታገድም ። የሀገሪቱ የምርጫ ህግ እስካልተሻሻለ ድረስ የምርጫ ቅስቀ,ሳ እንደማያደርግ አስረግጦ አስታውቋል። 
ፓርቲው በዚሁ ጥያቄው ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን እንዲመሰረት፣ በጎርጎርሳዉያኑ 2013 የተቋረጠው የህገ-መንግስት መሻሻል  ሂደት እንዲነቃቃ ፣ ነፃ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎችን የሚፈቅዱ የህግ ለውጦች እንዲደረጉ እንዲሁም የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የዳኝነት ግምገማ እና ፕሬዝዳንት ሆኖ የሚያሸንፈው ዕጩ  አ ቢያንስ 51% ድምጽ እንዲያገኙ የሚያስገድድ መስፈርት እንዲሟሉለት ጠይቋል።

ጀርመን የታንዛንያ ቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ በደሎች
ነገር ግን ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን የሚመሩት የታንዛንያ መንግስት ለዋነኛው ተቀናቃኝ ፓርቲ ጥያቄ መልስ መስጠት የፈለገ አይመስልም። የፓርቲውን መሪ ዘብጥያ ከመውርወር ባሻገር ፓርቲው እስከ 2030 ከማንኛውም ምርጫ ታግዶ እንዲቆይ በፍርድ ቤት አስወስኖበታል።
ውሳኔው ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሻገር ቀጣናዊ እና ዓለማቀፋዊ ትችት ማስከተሉ ግን አልቀረም። ከስድስት ወራት ብዙም ያልራቀ ጊዜ የቀረው የታንዛንያ ምርጫ ከዋነናው የተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ ውጭ ይካሄድ ይሆን ወይስ የታንዛንያ መንግስት ዉሳኔውን ቀልብሶ ለንግግር እና ድርድር ዕድል በር ይከፍ ይሆን ? ጊዜው ሲደርስ ይታያል ።

ታምራት ዲንሳ 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW