የችግኝ ተከላ እና የአድማጮች አስተያየት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 2007ማስታወቂያ
ለዚህም በብዛት ዛፎችን መትከል ይገባል በሚል የሚበረታታዉ። ዛፎችን የመትከሉ አስፈላጊነት ቢታመንም በዘመቻ በሚከናወኑ የችግኝ ተከላዎች የሚተከለዉን ብዛት ያህል ለዉጤት አለመብቃታቸዉ ብዙዎች የሚያነሱት እዉነት ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት 3 ቢሊዮን ችግኝ በዘንድሮዉ ክረምት ተተከለ መባሉን በማስመልከት ያቀረብነዉን ዝግጅት ስናጠናቅቅ እናንተ አድማጮቻችን በየአካባቢዎቻችሁ ያስተዋላችሁትን እንድታካፍሉን ጋብዘን ነበር። ከአርባ የሚበልጡ አድማጮችም በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ አስተያየታቸዉን አስፍረዋል። በድምፅም አስተያየታቸዉን የሰጡን አሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ