የኃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመነጋገር ጥያቄ አቅርበዋል
ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2012
ማስታወቂያ
ትናንት ወደ መቀሌ የተጓዘው የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ስብስብ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመነጋገር ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።
ሽማግሌዎቹ ግንቦት ወር ላይ ጥያቄዎች ሁሉ በንግግርና በሰላም መፈታት አለባቸው በሚል በስፋት ውይይት አድርገው እንደነበርና ፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይና በፌደራል መንግስት መካከል የሚስተዋለው ፍጥጫ ወደ ግጭት የማምራት አዝማሚያ በማሳየቱ ቅድሚያ እንደተሰጠው ተገልጿል። ሽምግልና ላኪ እና ሽምግልና ተቀባይ በማይኖርበት ሀገር ችግር ውስጥ ከመግባቷ በፊት ለመታደግ በራሳቸው ተነሳሽነት እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት አስታውቋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ