1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የስፖርት መሰናዶ

ሰኞ፣ ነሐሴ 14 2010

በ2019 ለሚካሔደው የአፍሪቃ የ17 አመት በታች የእግር ኳስ ዋንጫ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ አገሮች የማጣሪያ ጨዋታዎች በመካሔድ ላይ ይገኛሉ። ውድድሩን እየተከታተለ የሚገኘው የሶከር ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ አርታኢ ኦምና ታደለ ኢትዮጵያ ጅቡቲን 4:0 ደቡብ ሱዳንን 5:1 ብታሸንፍም ሀገራቱ "ቀላል ግምት" የተሰጣቸው እንደነበሩ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል

FC Barcelona vs. Boca Juniors | Philippe Coutinho
ምስል picture-alliance/NurPhoto/X. Bonilla

ስፖርት፣ የነሀሴ 14 ቀን፣ 2010 ዓም

This browser does not support the audio element.

በሚቀጥለው ዓመት ለሚካሔደው የአፍሪቃ ዕድሜያቸው ከ17 አመታች የሆኑ ወጣቶች የእግር ኳስ ዋንጫ የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ አገሮች የማጣሪያ ጨዋታዎች በታንዛኒያ በመካሔድ ላይ ይገኛሉ። ዕድሜያቸው ከ17 አመት በታች የሆኑ የአፍሪቃ ወጣቶች በሚሳተፉበት ውድድር ለማለፍ ኢትዮጵያ በመካከለኛው እና ምሥራቅ አፍሪቃ ቀጠና ተደልድላለች። የዘንድሮው የኢትዮጵያ የወጣቶች ብሔራዊ ቡድን እንደ ከዚህ ቀደሙ የዕድሜ ውዝግብ አልገጠመውም። በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው የአዳጊዎቹ ብሔራዊ ቡድን ሶስት ጨዋታዎች አሸንፎ ምድቡን በበላይነት እየመራ ይገኛል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በቀላሉ ማሸነፍ ችሏል። ውድድሩን እየተከታተለ የሚገኘው የሶከር ኢትዮጵያ ድረ-ገጽ አርታኢ ኦምና ታደለ ብሔራዊ ቡድኑ ጅቡቲን 4 ለዜሮ እንዲሁም ደቡብ ሱዳንን አምስት ለአንድ ማሸነፍ ቢችልም ሀገራቱ በምድቡ "ቀላል ግምት" የተሰጣቸው እንደነበሩ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል። በሁለቱ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ነው ወይም አይደለም ብሎ መመዘን እንደማይቻል የገለጸው ኦምና "ሁለቱ አገራት ያላቸው የእግር ኳስ ደረጃ እና ይዘዋቸው የሚመጧቸው ቡድኖች ደካማ" መሆናቸውን አስረድቷል።  በዛሬው የስፖርት መሰናዶ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጀርመን ቡንደስሊጋን የተመለከቱ ዘገባዎች ተጠናቅረውበታል። 
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW