1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርትኢትዮጵያ

የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ታዳጊዎች ተመረቁ

ቅዳሜ፣ መስከረም 12 2016

"ብሩህ ትውልድ" የተባለውና በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ግዛት ተመስርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በልዩ ልዩ ክህሎቶች ላይ ስልጠና የሚሰጠው ድርጅት ለሦስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ አስመረቀ።

Äthiopien | Ausbildung von Jugendlichen
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ኢትዮጵያዊያን በጎ ፈቃደኛ መምህራን የተሳተፉበት የነጻ ትምህርት ዕድል ተመራቂዎች

This browser does not support the audio element.

ነፃ ትምህርት ለ ታዳጊዎች

"ብሩህ ትውልድ" የተባለውና በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ግዛት ተመስርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በልዩ ልዩ ክህሎቶች ላይ ስልጠና የሚሰጠው ድርጅት ለሦስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ አስመረቀ።
ተቋሙ እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑትንና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በቋንቋ፣ በአስተሳሰብ ክህሎት፣ በተግባቦት ፣ በአመራርነት እና ሌሎችም ዘርፎች በመላው ዓለም በበጎ ፈቃድ በሚሳተፉ መምህራን በበይነ መረብ የ12 ሳምንታት ስልጠና ሲሰጥና ሲያስመርቅ ይህ ሦስተኛ ጊዜው ነው ተብሏል።
ከሁለት የድርጅቱ መስራቾች አንዷ የሆኑት ዶክተር ፀጋ ሰለሞን ዕድሉን የሚያገኙት ተማሪዎች ከቤተሰብ አልፎ እንዴት የቀጣይ ትውልድ የሀገር ተረካቢ መሆን ይችላሉ በሚለው ዙሪያ ተጨባጭ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር የሥራቸው ዋነኛ ግብ መሆኑን ገልፀዋል።ዲግሪያችንን አላገኘንም የሚሉ ተመራቂዎች አቤቱታ
በዶክተር ብርሃኑ ቡልቻ እና በዶክተር ፀጋ ሰለሞን ከ ሁለት ዓመታት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተመሰረተው "ብሩህ ትውልድ" የተባለውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት በውጪ ሀገራት የሚኖሩ በማስተማር ሙያ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ከ በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪዎችን በበይነ መረብ ልዩ ልዩ ክህሎቶችን እያስተማረ መሆኑን አስታውቋል።
ይህ የሦስተኛው ዙር የክህሎት ትምህርት ከተሰጠባቸው 33 ማዕከላት መካከል ከሆሳዕና የመጣው የ 11 ኛ ክፍል ተማሪ ሮቤል ኢያሱ አንዱ ሲሆን አገኘሁት ከሚለው ከብዙ በጥቂቱ በራስ የመተማመን ብቃቱ ማደጉን ይግልፃል።
"በዚህ ፕሮግራም ውስጥ የተማርኩት ነገር እንዴት ከሰው ጋር መነጋገር፣ መኖር እንደሚቻል አውቂያለሁ"
ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ላይ የጠለቀ የትምህርት መረዳት እንዲኖራቸው እየሠራ መሆኑን የገለፀው ድርጅት እስካሁን ባደረጋቸው ስልጠናዎች 1000 ተማሪዎችን ማስተማሩን ገልጿል።
የምልመላ መስፈርቱን አልፈው ከገቡ ተማሪዎች መካከል ከደብረ ብርሃን የመጣችው ቅድስት አረጋ ትገኝበታለች።"እዚህ ፕሮግራም ላይ በምሳተፍበት ጊዜ የግጭት አፈታት ክህሎቶችን አግኝቻለሁ"
ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የተመረጡ ጎበዝ የሁለትኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይህንን እድል ያቀረበው ብሩህ ትውልድ በሂደት ተማሪዎች በላቀ ቁጥር እድል እንዲያገኙ ጥረት እንደሚያደርግ ከመስራቾች አንደኛዋ ዶክተር ፀጋ ሰለሞን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ ከነደፋችሁት ትምህርት በላቀ ግጭት አፈታት፣ በመከባበር ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ድርጅታችሁ ምን ጥረት አድርጓል ያልናቸው ዶክተር ፀጋ ሥነ ምግባር ተማሪዎቹ እንዲማሩ ከሚደረግባቸው ዘርፎች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል።
"እርስ በርስ ተስማምቶ፣ ተነጋግሮ አንድ ነገር ማስፈፀምን፣ እውነተኛ ፣ ሀገር የሚወድ ትውልድ ነው የምንረዳቸው"
ከየትኛውም መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንደሌለው ያስታወቀው ይህ ድርጅት ወጪውን በበጎ ፈቃደኞች እንደሚሸፍንና በማስተማር ላይ የሚሳተፉ 100 በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን አስተማሪዎችን ከመላው የዓለም ዳርቻ ማሰባሰብ መቻሉንም አስታውቋል።

የሦስተኛው ዙር የክህሎት ትምህርት ከተሰጠባቸው 33 ማዕከላት መካከል ከሆሳዕና የመጣው የ 11 ኛ ክፍል ተማሪ ሮቤል ኢያሱ አንዱ ሲሆን አገኘሁት ከሚለው ከብዙ በጥቂቱ በራስ የመተማመን ብቃቱ ማደጉን ይግልፃል።ምስል፦ Solomon Muchie/DW
ተቋሙ እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑትንና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በቋንቋ፣ በአስተሳሰብ ክህሎት፣ በተግባቦት ፣ በአመራርነት እና ሌሎችም ዘርፎች በመላው ዓለም በበጎ ፈቃድ በሚሳተፉ መምህራን በበይነ መረብ የ12 ሳምንታት ስልጠና ሲሰጥና ሲያስመርቅ ይህ ሦስተኛ ጊዜው ነው ተብሏል።ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW