የኑሮ ውድነት በኢትዮዽያ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 26 2002ማስታወቂያ
ብር የመግዛት አቅሙ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኑሮውን ሁኔታ ወደባሰ መስመር እንደሚወስደው ባለሙያዎች ይናገራሉ። በኢትዮዽያ በአሁኑ ጊዜ ኑሮ እየናረ እንደመጣ አብዛኛው ሰው ሲናገር ይሰማል። መንግስት የዋጋ ግሽበት መጠን ከዜሮ በታች ደርሷል እያለ በሚገልጽበት በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ ዕቃዎች በተለይም ለምግብነት የሚውሉት ዋጋቸው በአብዝኛው በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ህብረተሰቡ በምሬት ይገልጻል። ከተለያዩ የኢትዮዽያ አከባቢዎች ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ኑሮ ከአቅም በላይ ሆኗል።
መሳይ መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ