ባህላዊ ግጭት አፈታት ዜዴ በኑዌርና አኙዋ ብሔረሰብ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 24 2017
ባህላዊ ግጭት አፈታት ዜዴ በኑዌርና አኙዋ ብሔረሰብ
በጋምቤላ ክልል የኑዌርና አኙዋ ብሔረሰብ የየራሳቸው ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ አላቸው፡፡ ይህ የግጭት አፈታት ዜዴም ህብረሰተቡ ለዘመናወት ሲጠቀምባቸው የኖረ እና ከግለሰብ እስከ ጎሳ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን የሚፈቱበት አሰራር እንደሆነ የየብሔረሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት ሳይደርሱ በርካታ ጉዳያዎች በባህላዊ መንገድ በመፍታት በገጠራማ አካባቢዎች ህብረተሰቡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴን እየተገለገሉበት እንደሚገኙም ተገልጸዋል፡፡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴውም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በቶሎ ከመፍታት እና ዘመናዊውን የፍትህ ስርዓት በማገዝ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የክልሉ ባህልና ቱርዝም አመልክተዋል፡፡
‹‹ዊርኩር›› የአኙዋ ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ
በክልሉ ከሚገኙት የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች መካከል የኑዌርና አኙዋ ብሔረሰቦች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሁለቱ ህዝቦች በክልሉ ሰፊ መልክአ ምድርን የያዙና በህዝብ ቁጥርም ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው ሲሆን በሚኖሩበት አካባቢ የየረሳቸው ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴያላቸው ናቸው፡፡ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን እና የነዌር ብሄረሰብ ዞን ውስጥ የሚኖሩት ሁለቱም የማህበረሰብ ክፍሎች ግጭቶች ሲከሰቱ ችግሩ ሳይፋፋ መፍትሄ የሚያገኝበት ይህ ባህላዊ ዜዴ ለዘመናት በሰዎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታት እና ቁርሾን በመቀነስ ማህረሰቡ ሲጠቀምበት እንደነበር የብሄረሰቡ ሀገር ሽማግሌዎች ይናገሩ፡፡
‹‹ዊርኩዎር›› የተባለው በአኙዋ ብሄረሰብ ዘንድ የሚታወቀው ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴም ለዘመናት ህብተሰቡ ሲጠቀምበት የነበረ እና አሁንም በስፋት እየተጠቀመበት እንደሚገኝ በአኙዋ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ኦዶል አጉዋ አመልክተዋል፡፡ ይህ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ በብሔረሰቡ ውስጥ ቅሚ በቀልን በማስወገድ ግጭት ሲከሰት በቀላሉ የሚፈታበት መንገድ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት የግጭቱን መንስኤዎች በማየት በተለያዩ ደረጃዎች እልባት እንዲያኙ ይደረጋል፡፡ የተፈጸመው ድርጊት ዓይነት ላይ በበመርኮዝ የቅጣት መጠኑም የሚለያይ እንደሆነ አቶ ኦዶል አብራርተዋል፡፡
‹‹ኮሮ›› በአኙዋ ብሔረሰብ ባህላዊ መሪ
በግጭት ወቅት በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት እንደ ህይወት ማጥፋት ወንጅሎች ሲፈፈሙ በብሄረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ወደላቸው ‹‹ኮሮ›› ወደ ተባለው መሪ ጉዳዮን በማቅረብ እንዲታይና እልባት እንዲያገኝ ይደረገባል ብሏል፡፡ በኮሮ መሪ በኩል የተጎጂ ቤተሰብ እና ጉዳት ያደረሱት ወገን በመቀራረብ በባህሉ መሰረት ተገቢውን ካሳ በመክፈልና ሌሎች ቅጣቶችን በመቀበል ዕርቅ እንዲወርድ ይደረጋል፡፡
በአኙዋ ብሔረሰብ ባህል ‹‹ቡራ›› ወይም ሸንጎ በተባለው ስርዓት ከሁለቱም ወገኖች ሽማግሌዎች በማሰባበስ በዚሁ ባህላዊ ስርዓት ዕቀር እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ በህብረሰቡ ባህል መሰረት ካሳው ተከፍለው ስርዓቱ ይጠናቀቃል፡፡ በከዚህም በተጨማሪም አቶ አዶል እንደሚሉት ቅሚ በቀል እንዳይከሰትና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደረስ በህብረተቡ ባህል መሠረት ‹‹ጎርቶንግ›› የተባለ የመሐላ ስርዓት ይፈጸማል፡፡
የኑዌር ብሔረሰብ የግጭት አፈታት ስርዓት
በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የራሳውን ባህል ያላቸው ሲሆን በክልሉ በስፋት ከሚገኙት መካከል አንዱ የሆነው የኑዌር ብሄረሰብ ዘንድም ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ የተለመበደና ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው እንደሆነው የብሔረሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ በኑዌር ብሔረሰብ ውስጥ የሚታወቁ አራት ጎሳዎች ያሉ ሲሆን በጎሳ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በብዛት ከዘመናዊ የህግ ስርዓት ይልቅ ‹‹ኳር ሙን›› ወይም ‹‹ቾድ›› በተባለው ባህላዊ የግጭት አፈታት አሰራር ችግሮችን እንደሚፈቱ በኑዌር የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ፒተር ጋትዌች አብራርተዋል፡፡ በዚህ ባህላዊ አሰራር በግለሰቦች፣በቡድን መካከል የተከሰቱ ማንኛውንም ግጭት፣ስርቆት እና ግዲያ ወንጀሎችን ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮችን የሚመለከት ስርዓት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በእርሻ፣በዓሳ ማስገር እና በተለያዮ የስራ ዘርፎች የሚተዳደረው የኑዌር ህዝብ በብሄረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶች በሁለት መንገድ የሚታዩ ሲሆን አንደኛ በቤተሰብ ወይም ዘመድ አዝመድ መካከል የተከሰቱ እና በጎሳ መካከል የተከሰቱ ግጭቶች የሚፈቱበት የራሳቸው አሰራር አላቸው፡፡ አቶ ፒርት እንዳብራሩት ከቤተሰብ ግጭት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ወንጀል የተባሉ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ረዋል እና ኳር ሙን ተብሎ በሚታወቁት ባህላዊ ዘዴ ይታያሉ፡፡ ‹‹ሩዋል›› በበተሰብ መካከል የተከሰቱ ግጭቶችን በቀላሉ የሚፈታ ሲሆን
‹‹ቾድ›› ደግሞ በጎሳ መካከል የተከሰቱትን ግጭቶች ወደ ፍርድ ቤት ሳይደርሱ የሚፉተበት አሰራር ናቸው፡፡
በኑዌር ብሄረሰብ ባህል መሰረትምበግጭት ወቅት ጉዳት ያደረሰው አካል ለእረቅ ካሳ መክፈል የሚጠበቅበት ሲሆን የሚከፈልው ካሳ ለአብትም ህይወት የማጥፋት ወንጅል ከሆነ በድርጊቱ የተሳተፈ አካል እንዲያዝና ለብቻ እንዲቆይ ወይም እንዲታሰር ይደረጋል፡፡ ለተጎጂ በተሰቦች እና ድርጊቱን የፈጸመው አካል በተሰቦች ደግሞ በባህሉ መሰረት በተመሳሳይ ካሳ በመክፍል ዕርቅ እንዲወርድ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በጎሳ መካከል ለተፈጠረው ግጭት ለግዲያ ወነጅል አስከ 200 ከብቶችን ካሳ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን በቤተሰብ መካከል ለተፈጠሩ ግጭቶች ደግሞ የካሳው መጠን ይቀንሳል፡፡
የጋምቤላ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ባህላዊ እሴቶችን ለማቆየትና ለትውልድ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴን ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ከፍሎች በሚኖሩበት አካባቢ የሚገለገሉባቸውን ማህበራዊና እና ፖለቲካዊ ዜዴዎችን፣ ኑሮአቸውን ለመምራት የሚገለገሉባቸውን ደንቦችና እና እሴቶችን በመሰድ በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙ ቢሮ አመልክተዋል፡፡
ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜም በክልሉ ግጭቶች ሲከሰቱና በህብሰረተቡ ውስጥ የሚከሰቱ ውስብስብ ችግሮችን በመፍታት ዘመናዊውን የፍትህ ስርዓት በማገዝ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገልጸዋል፡፡ በጋምቤላ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ መንግስቱ ከበደ ተቋሙ በክልሉ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴን ጨምሮ የተለያዩ የባህል እሴቶችን እንደሚገኙ በመጥቃስ እያንዳንዱ ማህበረሰብ የየረሳቸው የግጭት አፈታት ዜደ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
በኑዌር ብሄረሰብ ባህል ከቤተሰብና በጎሳ ደረጃ የሚነሱ ግጭቶችን የሚፈቱበት እና ከመደበኛ ፍርድ ቤት ይልቅ በገጠራማ ቦታዎች ህብረተሰቡ እየተገለገለበት እንዲገኙ አመልክተዋል፡፡ በአኙዋ ብሔረሰብም እንደዚሁ ከስርቆት ጀምሮ በበድን መካከል የሚከሰትን ግጭት የሚፈቱበትን ባህላዊ ስርዓት ማህበረሰቡ በሚኖርሩባቸው አካባቢዎች እየተዳኙበት ይገኛሉ ብሏል፡፡ በተለይ በጎሳ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ በባህላዊ መንገድ የሚሰጡት መፍትሄዎች ግጭቶች እንዳይባባሱ ከማድረግ እና በቶሎ እልባት እንዲሰጥ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ እገዛ እያደረገ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በጋምቤላ የተለያዩ የማህረሰብ ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን በክልሉ አምስት የሚደርሱ ብሄረሰቦች የየራሳቸውን የግጭት አፈታት ዜዴ እንዳላቸው ተገልጸዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር