የናዚ ጭፍጨፋ ሰለቦች ታስበዉ ዋሉ
ዓርብ፣ ጥር 19 2015
ማስታወቂያ
የናዚ ጭፍጨፋ ሰለቦች መታሰብያ
የጀርመን ፓርላማ «ቡንዴስታግ» በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት የናዚ ጭፍጨፋ ሰለቦችን አስቦ ዋለ። የጀርመን ፓርላማ በዛሬዉ እለት በናዚ ጀርመን በተለይ በአናሳ ፆታነታቸዉ ሰለባ የሆኑት ነዉ አስቦ የዋለዉ ። ዘንድሮ 78 ኛ ዓመትን ያስቆጠረዉን ናዚ የግፍ ጭፍጨፋ፤ በጀርመን እለቱ ሰለቦችን ማሰብ በይፋ ማሰብ የተጀመረዉ ከጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓም ጀምሮ ነዉ ። በየዓመቱ በዛሬዉ እለት ማለትም በጎርጎረሳዉያኑ ጥር 27 የናዚ ጀርመን ጭፍጨፋ ሰለቦች በጀርመን ዉስጥ በተለያዩ መታሰብያ ዝግጅቶች ታስበዉ ይዉላሉ። የጀርመን ፓርላማ የቡንዴስታግ ፕሬዚዳንት ባርቤል ባስ ዛሬ በፓርላማ ላይ በተካሄደዉ የመታሰብያ ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በጀርመን የናዚ ጭፍጨፋ ካከተመ በኋላም ግብረ ሰዶማውያን፣ እና ሌሎች አናሳ የተባሉ ሰዎች በማንነታቸዉ መሳደዳቸዉ መቀጠሉን አስታዉሰዋል።
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ