1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገሮች ጉባኤ ያለስምምነት ፊርማ መጠናቀቁ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 22 2001

የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ጉዳይ በተፋሰሱ ሐገራት ዘንድ ዛሬም እልባት አላገኘም። አሌክዛንድሪያ ግብፅ ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ ግብፅና ሱዳን ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ስምምነቱ ሳይፈረም በይደር ለስድስት ወራት ተራዝሟል።

ምስል RIA Novosti

አስሩ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀገሮች የውሀ ሀብት ሚንስትሮች በግብፅ አሌክዛንድሪያ ከተማ ያካሄዱትን ጉባኤ አጠናቀዋል። ሆኖም የያዙት ጉባኤ ስምምነቱ ከስድስት ወር በኋላ እንደገና ሊታይ ሳይፈረም እንደቀረ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ ዘግቧል። የስምምነቱ ፊርማ የመራዘሙ ምክንያት ግብፅና ሱዳን ከወንዙ የምናገኘው ድርሻ ሊቀንስብን ይችላል በማለታቸው እንደሆነም ተዘግቧል። የተፋሰሱ የልማት ዕቅድ ዋና ቢሮ በሱዳን ካርቱም ከተማ በሚገኘው የአካባቢ ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ/ማንተጋፍቶት ስለሺ/አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW