1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔቶ አባል ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ፍጻሜ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 6 2015

የኔቶ መሪዎች በጉባኤያቸው ለዩክሬን ተጨማሪ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ጦርነቱን በድል እስከሚጠናቀቅ ለመስጠት ቃል ከመገባት ጀምሮ፤ ከጦርነቱ ማብቃት በኋላም በሁሉም መስክ ድጋፍ ለማድረግና የደህንነት ዋስትና ለመስጠት የሚያስችሉ ስልቶች እንዲቀየሱ ተስማምተዋል።ይሁን እንጂ ዩክሬን የድርጅቱ አባል የምትሆንበትን ግዜ አልቆረጡም።

NATO-Ukraine Council
ምስል Aytac Unal/AA/picture alliance

የኔቶ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ፍጻሜ

This browser does not support the audio element.

ላለፉት ሁለት ቀናት በሉትዋኒያ ቪልኒዩስ የትካሂደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል አገሮች የመሪዎች ጉባኤ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጹል። የዩክሬንን ጉዳይ ዋና አጀንዳው አድርጎ የተሰየመው ይህ 31 መሪዎች የተሳፉበት ጉባኤ፤ ዩክሬን ከሩሲያ  ጋር የገጠመችውን ጦርነት በአሸናፊነት እንድትወጣ ማንቸውንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቶና በሩሲያ አንጻርም አንድነቱን አጠናክሮ የተነሳ ስለመሆኑ በስፊው እይተዘገበ ነው። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ሚስተር ያንስ ስቶልቴንበርግ የጉባኤውን ማብቃት ተከትሎ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተላለፉትን ውስኔዎችና የጉባኤውን ስኬት ባጣቃልይ አስርድተዋል።«ሁለት ቀናት በቆየው ጉባኤ  በድርጅቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ውሳኝ የሆኑ  ውሳኒዎች ተላልፈዋል ከሁለተኛ አለም ጦርነት ወዲህም ጠንካራና ዝርዝር የመካላክያ እቅድ ላይ፤ ከስምምነት ተድርሷል። መክላካያችንን ለማጠንከርና ለዩክሬን የሚደረገውን ድጋፍ ለማሳደግና ዩክሬንንም ወደ ድርጅቱ እንድትቀርብ ለማድረግ እንዲሁም ሁለቱ በአቻነት የሚሳተፉበት የዩክሬንና ኔቶ ካውንስል የተቋቋመ መሆኑንም ገለጸዋል። ሚስተር ስቶልቴንበርግ እስክሁን ለዩኪረን በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር እርዳታ ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም አባል አገርራት ተጨማሪ አዳዲስ እርድታዎችን ለመለገስ ቃል የገቡ ማሆኑን አስታውቀዋል።

ምስል Mindaugas Kulbis/AP Photo/picture alliance

በጉባኤው በተጋባዥነት የተገኙት  የጃፓን፤ አውስትራሊያ፤ ኒውዝላንድና ደቡብ ኮሪያ መሪዎችም ለዩክሬን የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። የኔቶ መሪዎች  ከነዚህ የኢንዶ ፓስፊክ አገሮች መሪዎች ጋርም  በአካባቢው ስላለው ስጋትና በጋራ መስራትም ስለሚችሉበት ሁኔታ የተወያዩ መሆኑንም ዋን ጸህፊው አስታውቀዋል |’ ኔቶ አካቢያዊ  ድርጅት  ቢሆንም ተግዳሮቶቹ ግን አለማቀፋዊም ጭምር ናቸው’ በማለት በአውሮፓ ያለው ችግር የኢንዶ ፓስፊክ አገሮችንም ይመለክታል የነሱም እኛን ይመለክታል በማለት ኔቶ ከቀጠናዊ  ጉዳዮች አልፎ በአለማቀፍ  በተለይም በኢንዶ ፓሲፊክ አካባቢ ባሉ ችግሮች ላይም ከነዚህ አገሮች ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎትና ጅማሮ ይፋ ድርገዋል ።፡ ከኢንዶ ፓስፊክ  አገሮች ጋር ኔቶ እየፈጠረው ያለው  ግንኑንተና ትብብር በተለይ አሜሪካ ከቻይና ጋር በገባችበት ውጥረት ድርጅቱን የሚከት እንዳይሆን የሚሰጉ አገሮች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን፤  ፈረንሳይ በጃፓን ሊከፈት የታሰበውን የድርጅቱን ቢሮ መቃውሟም በዚህ ምክኒያት ስይሆን እንዳልቀረ ነው የሚገመተው። የኔቶ መሪዎች በጉባኤያቸው ለዩክሬን ተጨማሪ ዘመናዊ  የጦር መሳሪያውፕችን ጦርነቱን በድል እስከሚጠናቅቁ ለመስጠት  ቃል ከመገባት ጀምሮ፤ ከጦርነቱ ማብቅት በኋላም በሁሉም መስክ ድጋፍ ለማድረግና የደህንነት ዋስትና ለመጠት የሚያስችሉ ስልቶች እንዲቅየሱ  ተስምምተዋል ። ይሁን እንጂ  ዩኪረን የድርጅቱ አባል የምትሆንበትን ግዜ  አልቆረጡም። ስለዩክሬን የኔቶ አባልነት ከድርጅቱ የወጣው መግለጫ  “ የአባልነት መስፈርቶች የተሟሉ መሆናቸው ስረጋግጥና በዚህም አባሎች ሲስማሙ ያኔ ለዩክሬን የባልነት ግብዣ የሚላክ የሆናል’ የሚል ሲሆን ይህም የዩክሬንን ባስልጣኖች ማስክፋቱ ታውቁል።
ይሁን እንጂ የሰባቱ የበልጸጉ አገሮችም  በበኩላቸው በተጓዳኝ በሰጡት መግለጫ  ለዩክሬን የተለየ ድጋፍ እንደሚይደርጉ ቃል በመግባታቸውና  የኔቶ አገሮችም ከአባልነት በመለስ ለዩክሬን የማይሰጡት እርዳታ የማይኖር መሆኑን በማሳወቅቸው፤ የክሬን መሪዎች በጉበኢው ውጤት ረክተዋል  ተብሏል።  በአጠቅላይም የዩክሬይንና ሩስያ ጦርነት፤ አባል አገራቱን እያስከፈላቸው ካለው ከፍተኛ ዋጋ አንጻርና የጦርነቱ መጨርሻም አለምታወቁ፤  ልዩነቶች ሊፈጠሩና አንድነታቸውም ሊላላ ይችልል ተብሎ በአንዳንዶች ተገምቶ  የነበረ ቢሆንም ለግዜው ግን ጉባኤው ተሳክቶና አባል አገራቱም አንድትታቸውን አጠናክረው እንደወጡ ነው በሰፊው የሚነገረው። ፕረዝዳንት ባይደን ከጉባኤው በኋላ  ባደረጉት ንግግርም፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጦርነቱን ሲጀምሩ  ኔቶ የሚፈካከስና የሚዳከም መስሏቸው የነበር ቢሆንም ዛሬ ግን እውነታው ይህ አይደለም በማለት ይልቁንም ዛሬ ኔቶ  ከመቺውም ጊዜ ይበልጥ ጠነክራና ሀያል ሁኗል ብለዋል 
ሩሲያ የኔቶው ጉባኤ ያስተላለፈው ውሳኔና ለዩክሬን ሊሰጥ ያቀደው የመሳሪያ እርዳታ፤ ኔቶ በጦርነቱ በቀጥታ እየገባ መሆኑን የሚያመላክት ነው  በማለት፤ ይህም ድርጅቱ ወደ ቀዝቃዘዛው ጦርነት አስተሳሰብ እየተዘፈቀ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነና ለዚህም ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መገጫ አስታውቃለች።
ገበያው ንጉሤ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
 

ምስል Andrew Caballero-Reynolds/AFP/Getty Images
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW