1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው?

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 12 2017

"ትናንት መርካቶ ሄጄ ዕቃ ገዝቼ ነገ ደግሞ ስሄድ ጨምሮ ነው የሚገኘው። መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዳለ ጨምረዋል [ዋጋቸው]። ከሰላሙ አንጻር ነው እንጂ አዲስ አበባ ላይ ኑሮ ውድነቱ ምንም ደስ አይልም"።

"ለምሳሌ ቁርስ በልቶ ምሳ የማይደግም ሰው ሊኖር ይችላል። ሲቀጥል ደግሞ አንድ ነገር ሲጨምር እየጨመረ ነው እንጂ እየቀነሰ አይመጣም"።
"ለምሳሌ ቁርስ በልቶ ምሳ የማይደግም ሰው ሊኖር ይችላል። ሲቀጥል ደግሞ አንድ ነገር ሲጨምር እየጨመረ ነው እንጂ እየቀነሰ አይመጣም"።ምስል፦ Solomon Much/DW

አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው?

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት መተግበር ከተጀመረ አንድ ዓመት እየሞላው ነው። በዚህም የዛሬ ዓመት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ58 ብር ገደማ ይመነዘር የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላር 133 ብር ይመነዘራል።

ይህ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጉልህ የዋጋ ጭማሪ አስከትሎ በተለይ ቋሚ ደሞዝ በሚከፈላቸው ሠርተኞች ላይ ከፍተኛ የኑሮ ጫና ማሳደሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ለመሆኑ የኑሮ ውድነቱ ምን ይመሳል በሚለውን ላይ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት ጠይቀናል።

"የኑሮ ውድነቱ በተለይ በተለይ ወርሃዊ ደሞዝተኞችን በከፍተኛ ኹኔታ እየጎዳ ያለበት ኹኔታ ነው ያለው። ከዚያም ባለፈ ሀገሪቱ ላይ ያሉ የሰላም ሁኔት፣ የእንቅስቃሴ ገደቦች ተደምረው ለመኖር እጅግ አቸጋሪ ከሚባሉ ሀገራት ውስጥ ሆናለች ሀገራችን"

"ትናንት መርካቶ ሄጄ ዕቃ ገዝቼ ነገ ደግሞ ስሄድ ጨምሮ ነው የሚገኘው። መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዳለ ጨምረዋል [ዋጋቸው]። ከሰላሙ አንጻር ነው እንጂ አዲስ አበባ ላይ ኑሮ ውድነቱ ምንም ደስ አይልም"።

"ለምሳሌ ቁርስ በልቶ ምሳ የማይደግም ሰው ሊኖር ይችላል። ሲቀጥል ደግሞ አንድ ነገር ሲጨምር እየጨመረ ነው እንጂ እየቀነሰ አይመጣም"።
የሚሉ አስተያየቶች የተካተቱበትን ዝግጅት የማድመጫ ማዕቀፉን ተጭነው ያዳምጡ።
ሰሎሞን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW